OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Monday, April 20, 2015

ድረስለት ጌታ ለወገኔ – ሚኪያስ ቸርነት

ቅ/ሲኖዶስ: በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወገዘበሕይወቴ አይቼና ተሰምቶኝ በማያውቀው ሐዘንና የልብ ስብራት ዉስጥ ነኝ። አይ ኢትዮጵያዊ እንዲህ ሆነ ትቀር ? ? ? ? አገር እያለህ ተሰደህ፣ ምግር እያለህ ተረበህም ክብር እያለህ ተዋርደህ፣ ወገን እያለህ ብቸኛ ሆነህ ትቀር ? አገርህ የምድር ገሃነም ስለሆነችብህ ተሰደድክ። ኑሮን ለማሸነፍ፣ ግፍና ቀንበር ስለበዛብህ፣ ያንተንም የቤተሰቦችህን ኑሮ ለማሻሻል ተሰደድክ። የወንበዴና የጨካኝ ሰለባ ሆንክ። ስጋ የከበሱ ጭራቆቹ፣ ስጋህን አቃጠሉት። አንገትህን ቆረጡን። ግን ነፍስህን ሊነኳት አይችሉም።እነርሱ የዘላለም ገሃነም ይወርዳሉ። አንተ ግን ገነት ትኖራለህ። በዚያ ትንሽ ተጽናናው። ለምን ቢባል እግዚአብሄር ግፈኛን የሚሰብር ፣ የተገፋዉንም የሚያነሳ አምላክ ነውና። ስለኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ያገኛታል ተብሎም ስለተጻፈ።

No comments:

Post a Comment