OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Wednesday, March 18, 2015

የሰማያዊ አባል ከድብደባ ያተረፉትን የወጅ ህዝብን አመሰገነ

Tanaሰኞ መጋቢት ሰባት ቀን 2007 ዓ.ም ፣ በፎገራ ወረዳ ከወረታና ከአለምበር ከተማ መካከል 10 ኪሜ ርቀት
በምትገዉ ወጅ በምትባል የገጠር ከተማ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ቅስቀሳ ላይ በነበረበት ወቅት ተደበደበ!!
ኢህአዴግ ወያኔ ያሰታጠቃቸዉ ወንበዴዎች _ወለለዉ በላይነህ የሚባል ሚሊሻና _ጌታነህ የሚባል ፓሊስ _ኢህአዴግ በሰራዉ አስፓልት ሁነህ
አትቀሰቅስም በማለት የሚቀሰቅስበትን ማይክራፎን ወርዉረዉ ሰብረዉ የሚያስተዋዉቅበትን ፖስተር ቀደዉ ወጣቱን በአፈሙዝ በመምታት
በአስፓልቱ እየጎተቱ ሲወስዱት፣ የወጅ ከተማ ወጣቶች ተባብረዉ ከጉዳት ታድገዉታል።
የአካባቢዉ ነዋሪዎችም ሆ ብለዉ በመዉጣት መታወቂያዉን እንዳስመለሱለት ምንጮች አክለዉ አጋልጠዋል። ጉዳት የደረሰበት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ምንጮች ባነጋገሩበት ሰአት ለወጅ ከታማ ህዝብ እንዲህ በማለት ምስጋናዉን አስተላልፋል፦
«የነፃነት ቀናችን ቅርብ ናት።ለተባበራችሁኝና ከጎኔ ለነበራችሁ ወጣቶች ምስጋናየ ከፍ ያለ ነዉ።እንዲህ ከተባበርን አምባገነኖችን እናበረክካቸዋል።ድል
ለጭቁኑ ህዝባችን ዉድቀት ለዘረኛዉ ስርአት>
በደቡብ ጎንደር የአንድነት መዋቅር በብዛት ሰማይዊን የተቀላቀለ ሲሆን በዚያ ሰማያዊ ቢያንስ ወደ 11 ወረዳዎች፣ ተወዳዳሪዎችን እንደሚያሰልፍ ታውቋል። በዚያ ያሉ የብአዴን ካድሬዎች፣ ከፈረንጆች ተለምኖ በተሰራ፣ እነርሱን ግን ኢሕአዴግ ባሰራው አስፋልት የሙሉት ላይ እየሄዳችሁ መቀስቀስ አትችሉም ማለታቸው ምንም ያህል ሕዝቡን እናስተዳድራለን ብለው የተቀመጡት፣ ከስብእና በመዉረድ እንሳሳ እየሆኑ መምጣታቸዉን የሚያመላክት ነው።

No comments:

Post a Comment