OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Wednesday, September 28, 2016

በወልቃይት አዲ-ረመጽ በሚገኝ ሆቴል አማርኛ ዘፈን መከፈቱን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃ በመውሰዳቸው ውጥረት ቀሰቀሰ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)
ESATበወልቃይት አዲ-ረመጽ ከተማ የሚገኘ አንድ ሆቴል የአማርኛ ዘፈን በመከፈሩ የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት የሃይል ዕርምጃ በነዋሪዎች ዘንድ አዲስ ውጥረት መቀስቀሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ረቡዕ ለኢሳት አስታወቁ።
የትግራይ ክልል ልዩ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት በዚህ ዕርምጃ የሆቴሉ ባለቤት ልጅ ክፉኛ የድብደባ ድርጊት እንደተፈጸመበትና የከተማዋ ነዋሪዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል።
በአዲ-ረመጽ ከተማ የተቀሰቀሰውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ ነዋሪዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በመሰባሰብ ስራ እንዲስተጓጎል አድርገው መዋላቸውንም እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ከአመታት በፊት ያነሱት የማንነት ጥያቄ ህጋዊ ምላሽን አላገኘም በሚል ተደጋጋሚ ተቃውሞ በአካባቢውና በሌሎች የአማራ ክልል ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ይህንኑ የማንነት ጥያቄ ተከትሎ በትግራይ ክልል የጸጥታ ሃይሎች የሃይል ዕርምጃ ሲወሰድባቸው መቆየቱን ይገልጻሉ።
በአካባቢው ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ህጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ በማለት የጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ነዋሪዎች ተቃውሞን እያካሄዱ የሚገኝ ሲሆን፣ የፌዴራል ባለስልጣናት የወልቃይትን ጉዳይ በአማራና ትግራይ ክልሎች በኩል ዕልባት እንዲያገኝ ይደረጋል ሲሉ በቅርቡ አስታውቀዋል።

Monday, September 12, 2016

በወልቃይት ዐማሮች ላይ በአዲስ ዓመት ምሽት ተኩስ ሲዘንብባቸው አምሽቷል

ትናንት መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት በወልቃይት አዲ ረመጥ ከተማ አዲስ ዓመቱን የተወሰዉ ወገኖቻቸውን በማሰብ በቤታቸው ሲያከብሩ ውለዋል፡፡ ምሽት 3፡00 ሲሆን የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ የዐማራ ተወላጅ በሆኑ ቤተሰቦች ቤት ላይ ጥይት መተኮስ ጀመረ፡፡ የወልቃይት ወጣቶች ምንድን ነው በማለት ከቤታቸው ወጡ፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ሌሊት ድረስ በዐማሮች ላይ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን ወጣቶች የአጸፋ መልስ አልሰጡም፡፡
Wolqite News
ከአዲ ረመጥ ከተማ እኩለ ሌሊት ላይ መረጃውን የሰጡን ሰዎች በምን ምክንያት ይህ ተኩስ ሊፈጠር እንደቻለ ላነሳንላቸው ጥያቄ ‹‹ዛሬ የአዲስ ዓመት በመሆኑ ብዙ የወልቃይት ልጆች ይመጣሉ በሚል አስቀድሞ ዝግጅት ነበር፤ ወደ ምሽት አካባቢ መረጃው ደርሶናል፡፡ ምንም ዝግጅት ባላደረግንበት ወጣቶች የአጸፋ መልስ ሰጥተው ቢሆን ኖሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፖሊስ በተቀነባበረ ኦፕሬሽን ዐማሮችን በጅምላ ለመጨረስ የታቀደ ነው፡፡ ሆኖም አላስፈላጊ መስእዋትነት ላለመክፈል ወጣቶቻችን እንዲሸሹ አድርገናል፡፡ አሁን የሞተ ሰው ስለመኖር አለመኖሩ የምነግርህ ነገር የለም›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቶ ዘነበ ፋንታና አቶ ተስፋየ የተባሉ ዐማሮች እከለ ሌሊት ታፍነው ተወስደዋል፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ‹‹አዲስ ዓመት በሰላም የሚያከብረው ትግሬ ብቻ ሆኖ እስከመቼ እንደሚቀጥል የምናየው ይሆናል›› ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል፡፡

በደም እየተጠመቁ አዲስ ዓመት አይጠባም! – በላይነህ አባተ

14316857_1695388227454511_625065289199732991_nበአዲስ ዓመት ልጃገረዶች በአደይ አበባ፣ በጠልስም፣ በመስቀል፣ በድሪ፣ በአንባርና በአልቦ ተውበው አበባየሁ ሆይን ይዘምሩ ነበር፡፡ እነዚህ ልጃገረዶች ዛሬ ክር አስረው፣ ፊታቸውን ልጠውና ራሳቸውን ተላጭተው ለታረዱት ወንድሞቻቸውና አባቶቻቸው ሚሾ ያወርዳሉ፡፡ ጎረምሶች በአዲስ ዓመት ችቧቸውን አብርተው “በቆላ በደጋ ያላችሁ እንዴት ከረማችሁ?” እያሉ ሆያ-ሆየን ይጨፍሩ ነበር፡፡ ዛሬ እነዚህ ጎረምሶች መብት ስለጠየቁና የቅድመ አያቶቻቸውን ሰንደቅ ስለሰቀሉ እንደ በግ ታርደው ያሞራ ሲሳይ ሆነዋል፤ ካሞራ ሲሳይነት የተረፉትም ከርቸሌ ተጠብሰዋል፡፡ እናቶችና አባቶች በጳጉሜ ውኃ ተጠምቀውና ልባሳቸውን አጥበው አዲስ ዓመትን ይቀበሉ ነበር፡፡ የዛሬ እናቶችና አባቶች የታረዱና የተቃጠሉ ልጆቻቸውን በላስቲክ እንደ አዲስ ዓመት ስጦታ ተቀብለዋል፡፡
የታረዱና የተቃጠሉት ልጆቿ ደም ኢትዮጵያን ከፋሽሽት ዘመን የባሰ ጃኖ አልብሷታል፡፡ ከተከዜ እስከ ዓባይ፤ ከዓባይ እስከ አዋሽ፤ ከአዋሽ እስከ ሸበሌ፣ ከሸበሌ እስከ ገናሌ፣ ከገናሌ እስከ ባሮ ያሉ ወንዞቿ ደም ጎርሰዋል፡፡ ከወልቃይት እስከ ጎንደር፤ ከጎንደር እስከ ደብረታቦር፣ ከደብረታቦር እስከ ባህርዳር፣ ከባህርዳር እስከ ደብረ ማርቆስ፤ ከደብረማርቆስ እስከ አምቦ፣ ከአምቦ እስከ ደንቢ ዶሎ፤ ከደንቢ ዶሎ እስከ ወሊሶ፤ ከወሊሶ እስከ ቂሊንጦ፤ ከቂሊንጦ እስከ ዶዶላ፣ ከዶዶላ እስከ ያቤሎ ያሉ ኩሬዎች ደም ቋጥረዋል፡፡ ደም ያልነካው ውኃ እንኳን ለመጠመቂያ ለጸበልም ጠፍቷል፡፡ ይህንን ደም የጎረሰ ውኃ የማትያስ ሲኖድ የልማት ውኃ እያለ ወደ ሕዝብ ይረጨዋል፡፡ በኢትዮጵያ እሚወርደው የግፍ ዶፍ በጥፋት ውኃ፣ በሰዶምና ገሞራ ከጎረፈው የግፍ ዶፍም ከፍቷል፡፡
ከጥፋት ውኃንና ከሰዶም ገሞራ በኋላ ክርስቶስ ለፍትህ በመስቀል ተሰቅሏል፡፡ ክርስቶስ ለፍትህ የተሰቀለበትን መስቀል “አባ” ማትያስና ጳጳጳሳቱ ሳህን ሰርተው ፍትፍት ይዝቁበታል፤ ቪላ ገንብተው ይዘንጡበታል፤ ሉመዚን ቀጥቅጠው ይንፈላሰሱበታል፡፡ ፍትፍት ዘክዛኪውና በሉመዚን ተንፈላሳሹ አባ ማትያስና ተቋዳሽ ጳጳሳቱ “እስተንፋስ ያለው ሁሉ ይተንፍስና አትግደል” የሚሉትን ቃላት ሽረው “አትተንፍስ፤ አለዚያ ትሞታለህ” እያሉ ሟቹን ሲያስጠነቅቁ ይታያል፡፡ እነዚህ ፍትፍት ዘክዛኪዎች በሐዘን የተጎዳውን ሲያጽናኑና የታሰረውን ሲጠይቁ ሳይሆን በነፍሰ-ገዳይ ሰይጣኖች “ለሽምግልና” ታዝዘው ከነካባቸው ሲግበሰበሱ ይታያል፡፡ በሰማእታት አስከሬን ከበሮ እየመቱ እሚጨፍሩትን ሲያሳልሙ ይስተዋላል፡፡ አናባቢ ሆይ! ቤተመንግስትን ሰይጣን ቤተክርስትያንን ይሁዳዎች ነጥቀዋታል፡፡ በዚህም ምክንያት የግፉ ዶፍ አላባራ ብሏል፡፡ የማያባራው የግፍ ዶፍም እንኳን ወተትን ውኃ በማስሸፈት ይገኛል፡፡
ወተት ቀርቶ ውኃ በሚሸፍትበት ወቅት “እንኳን አደረሰህ” የሚባልለት አዲስ ዓመት አይኖርም፡፡ የገዳይ ደጋፊዎች በሲዳሞና በወለጋ ወርቅ ተሽቆጥቁጠው ከበሯቸውን እየወቀሩና እየዘለሉ በሰማእታት አስከሬን ስለጨፈሩ ሰዶምና ገሞራ እንጅ አዲስ ዓመት መጣ አይባልም፡፡ እነ ተከዜ፣ እነ አንገርብ፣ እነ ዓባይ፣ እነ ጨሞጋ፣ እነ አዋሽ፣ እነ ደዴሳ፣ እነ ባሮና ገናሌ ደማቸው ሳይጠራ አዲስ ዓመት አይነጋም፡፡ እነ ራስ ዳሽን፣ እነ ቋራ፣ እነ በላያ፣ እነ አመዳሚት፣ እነ ዝቋላ፣ እነ ጭላሎ የጎረምሶችን ሆያ-ሆየና የልጃገርዶችን አበባየ-ሆይ ሳያስተጋቡ አዲስ ዓመት አይጠባም፡፡ የሊማሊሞ ዳገት፣ የጣራ ገዳም ጋራ፣ የጮጨ ግርግዳ፣ የየረር ተራራ፣ የዓባይ በረሃ፣ የዋልድባ ገዳም፣ የዘጌ አድባራት፤ የሰብስቤ ዋሻ፣ የጋንቤላ ጫካ የሰማእታትን ጩኸት እያስተጋቡ አዲስ ዓመት አይከበርም፡፡ የማእከላዊ፣ የቃሊቲ፣ የቂሊንጦ፣ የዝዋይ፣ የሰንዳፋ፣ የብርሸለቆ፣ የአንገርብና የአሶሳ እስር ቤቶች የጦቢያን ልጆች ስቃይና ጣረ ሞት እየተመለከቱ አዲስ ዓመት አይከበርም፡፡
የዲያብሎስ ብሮድካሽን ኮርፖሬሽን(EBC=DBC) የሰማእታት ዓይን ሳይፈርስ አስረሽ ምቺው ስለጨፈረ አዲስ ዓመት ገብቷል አይባልም፡፡ “አባ” ማትያስ የምድርን ችሎት አምልጦ ከእግዜር ችሎት እንደቀረበው ወንድሙ “አባ” ገብረመድህን የደም ውኃን የልማት ጸበል እያለ ስለረጨ አዲስ ዓመት ተከበረ አይባልም፡፡ የለም! የለም! አዲስ ዓመት የለም፡፡ በፍልሰታና በጳጉሜ በደም እየተጠመቁ አዲስ ዓመት አይጠባም፡፡

መስከረም አንድ ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓ.ም.

Thursday, September 1, 2016

#ሰበር_ዜና- በዛሬዋ እለት በአሁኑ ሰአት ማምሻውን የመንግስት አየር ሀይል ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች የወልቃይት እና የአርማጭሁ አንዳንድ አካባቢወችን እየደበደቡ ነው -

14125510_1118124471628664_1667110904582126095_oነሐሴ 26/2008
በዛሬዋ እለት በአሁኑ ሰአት ማምሻውን የመንግስት አየር ሀይል ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች የወልቃይት እና የአርማጭሁ አንዳንድ አካባቢወችን እየደበደቡ ነው የሚል መረጃ እየወጣ ይገኛል።ይህ የመንግስት እኩይ ተግባር ያስቆጣቸው ያከባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞዋቸውን በጩኸትና በዋይታ በመግለፅ ላይ ናቸው ተብሎዋል።
ሕዝቤ ሆይ ያለን ብቸኛውና የመጨረሻው አማራጭ ራሳችንን ለማዳንም ሆነ ለመከላከል ጫካ ገብቶ ይሄንን አረመኔ ጠላት የሆነ መንግስት ተፋልሞ መጣል ብቻ ነው።
ተነስ አማራ ለወገንህ ድረስ!
The minority Ethiopian regime TPLF has started a full scale attack both by Air and ground military against amhara civilian in welkait and Armachiho gondar.
#AmharaGenocide #AmharaResistance
Amnesty International Human Rights Watch, BBC News Africa

ህወሀት ለእኔ እና ለአባቴ ቤት ዘላለማዊ ጠላት ናት

welkeit - satenaw 457ወያኔ በ1982 ወልቃይትን ወረረ ፣ አመፅ ሊያስነሱ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን ወጣቶች ወደ ትግራይ ባዶ ባዶ ስድስት ወደተሰኘው እስር ቤት ወረወራቻው እና አንድም ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሞት ቀጣቸው / አንዳንዶች በፀሀይ ብርሀን ማጣት አይነስውር ሆነው ከየት እና እንዴት መጣችሁ የሚላቸው ሳይኖር ትግራይ ጎዳናወች ለማኝ ሆነው ቀሩ / የተቀሩትን በግፍ እየገደለ ቀበራቸው ይህን ለማረጋገጥ አዲግራት ከአይነስውር ለማኞችን አንዱን መጠየቅ ይቻላል ።
ታሪክ አዋቂ የተባሉትን አዘውንቶች እየሰበሰቡ በጠላ ውስጥ በሚጨመር መርዝ በከላቸው አንዳንዶቹንም ተኩሶ ገደላቸው / የታማኝ በየነን የአውስትራሊያ ወልቃይት ቅሪቶችን ቃለ መጠይቅ ማዳመጥ ይቻላል /
ሴቶችን በግፍ እና ኢሰባዊነት በተሞላ ሁኔታ የማያውቁት የትግሬ ወንድ በወታደራዊ መኪና እየመጣ ሁሉንም ተራ በተራ ያስረግዟቸው ነበር / በቀላሉ አብዛኛውን ከ25 አመት በታች እድሜ ላይ ያለን የወልቃይት ተወላጅ ጠይቁ አባቱ ትግሬ ነው /የሚገርመው ዛሬ ግን ጠላት ሁኗቸው ተሰለፈ /
ያኔ እድሜየ 6 አመት ገደማ ነበር……..ብዙ የማላስታውሰው እና አባቴ ሲነግረኝ በደንብ ያልተረዳሁት ብዙ ነገር አለ ፡ እሱም እንዳልፈራ ሁሉንም አይነግረኝም ።
እንዲያ በግፍ ስንጠፋ እና ስንጨፈጨፍ ድረሱልን የምንልበት ምንም ነገር አልነበረም ስለዚህ ሞትን ዝም ብለን ሞትናት ።
ህወሀት ለእኔ እና ለአባቴ ቤት ዘላለማዊ ጠላት ናት ፤ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም መላ የአማራ ህዝብ ከህወሀት ጋር ቢታረቅ እንኳ እኔ በግሌ ሳልታልረቃት እቀራለሁ ።
~~~~የሰሜን ኮከብ~~~~