OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Tuesday, August 18, 2015

በቆሙበት የሚረግጡ ሰማያዊና መድረክ – ግርማ ካሳ

Bilderesultat for blue party ethiopiaBilderesultat for medrek party ethiopia“ፓርቲ አለኝ እያሉ አመታትን ከመቁጥር ግን ካአምባገነኖች ጋር ተጋፍጦ ፈርሶም ምስላቸዉን ማበላሸትና ጭምብላቸዉን ማስወለቅ ይሻላል፡፡አሁንም በህይወት ካሉት የጠፋን አንድነት ይፈራል ብሎኛል አንድ የዘመኑ ሰዉ….”
ይሄን የጻፊት አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው። ትክክለኛ አባባል ነው ያስቀመጡት። አቶ ተክሌ የእዉነተኛው የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ናቸው (ነበሩ ያላልኩት ወያኔ ሕጋዊነትን ቢወስድባቸው በአባላትና በደጋፊዎች ዘንድ አሁን እንደ መሪ ስለሚታዩ ነው) ።
እንደሚታወቀው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በኃይልና በጉልበት የአንድነት ሕጋዊነት ነጥቆ የድርጅቱን ሰርተፊኬት ራሱ ላደራጃቸው የትግስቲ አወሉ ቡድን መስጠቱ ይታወቃል። ወያኔዎች ሌሎች ድርጅቶችን ለማፍረስ አልሞክሩም። በትራቸው ያነሱት አንድነት ላይ ብቻ ነው። አንድነት በርግጥ በአገሪቷ በሙሉ ከፍተኛ ጥንካሬ የነበረው ድርጅት ነው። ሌሎች ድርጅቶች በሙሉ በአንድ ላይ ቢጨፈለቁ አንድነት ፓርቲን አያክሉም ነበር የሚል እምነት ነው ያለኝ።
አቶ ተክሌ እንዳሉት በርግጥ ፓርቲ አለን እያሉ ዝም ብሎ ከማውራት ሥራ ሰርቶ አምባገነኖችን ማጋለጥ ይቻላል። አንድነት ያደረገው ያንን ነው። አንድነት ፣ የፖለቲካ እርምጃ የተወሰደበት፣ ሥራ ስለሰራ ነው። ለዚህም አንድነቶች እና የአንድነት ደጋፊዎች ሊኮሩበት የሚገባ ነገር ነው።
አንድነቶች ፓርቲያቸውን ቢነጠቁም፣ ከትግሉ አልሸሹም። አንድነት ማለት የምርጫ ቦርድ ወረቀት አይደለም። አንድነት ማለት አባላቱ ፣ደጋፊዎቹ፣ ህዝቡ ማለት ነው።
ሰማያዊዎች አንድነት የሚሊዮኖሽ ድምጽ እንቅስቃሴ ያደረግ የነበረ ጊዜ እንኳን የትግል አጋርነት ሊያሳዩ፣ ጭራሽ ችግር ፈጣሪዎች ነበሩ። የአቶ ይልቃል ፖለቲካ የአብሮ መስራት ፖለቲካ ሳይሆነ ሌሎችን የማሳነስና የመከፋፈል ፖለቲካ ነበር። መድረኮች፣ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ እኛን ሳያስፈቅድ ለምን አደረገ ብለው ፣ አንድነትን ከመድረክ ዉስጥ አግደዉት ነበር።
በምርጫ 2007 ግን፣ አንድነቶች፣ ድርጅታቸው ቢታገድም፣ ትግሉ የድርጅት ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነው በሚል፣ ሰማያዊን፣ መድረክን በመደገፍ የትግሉ አካል ሆነው ሲንቀሳቀሱ ነበር።
በምርጫው ወቅት በተፌጠረው መቀራረብ ምክንያት፣ ሰማያዊን እና መድረክ በመደገፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አንድነቶች፣ አዲስ ፓርቲ አናቋቁምም በሚል ሰማያዊ ፓርቲን ወይንም መድረክን ለመቀላቀል ሐሳብ ነበራቸው። ሆኖም እንዳሰቡትና እንደጠበቁት የሆነለቻው አይመስልም።
የሰማያዊ ፓርቲ የአንድ ሰው ንብረት በመሆኑና ግትር ፖለቲካ በማራመዱ፣ ብዙ የአንድነት ኃይሎችን አቅፎ ማታገል አልቻለም። በአመራሩ ዘንድ ፍቃደኝነቱ ያለ አይመስልም። የተማሩ፣ የበሰሉ የአንድነት አመራሮች ሰማያዊን ከተቀላቀሉ እኛ ቦታችንን ልንለቅ እንችላለን የሚል ስጋት ሊቀመንበሩ ያደረበት ይመስላል። ሰማያዊ ሚስጥራዊ የሆነ፣ መሰረታዊ የሆነ የዲሞክራሲ አሰራር የሚጎድለው ድርጅት ነው። እጅግ በጣም የሚደነቁ፣ ጀግና ወጣቶችን አቅፏል። ሆኖም እነዚህ ወጣቶች በሳልና አስተዋይ መሪ አላገኙም። አሁን ያለው መሪ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደገና የዉሸት ምርጫ ተደረጎ ተመረጥኩ ብሎ ራሱን በራሱ በመሾም ብቅ እንደሚል ብዙ መጠራጠር የለብንም። አቶ ኃይሉ ሻወል ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ገለል ቢሉም በሌላ መልኩ ተመልሰው መጥተዋል። የአሁኑ የሰማያዊም መሪ ትንሹ ኃይሉ ሻወል መሆኑን በገሃድ እያሳየ ነው። እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ዉስጣዊ ዲሞክራሲ የሌለው፣ የአንድ ሰው አምባገነንነት የሰፈነበት ድርጅት ደግሞ የትም አይደርስም።
ምናልባት እዚህ የምጽፈው ስህተት ሆኖ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አመራር ይዞ ብቅ ካለ ፣ ያደርገዉ እንጂ፣ ለጻፍኩት ነገር ይቅርታ እንደምጠየቅ ለመግለጽ እወዳለሁ። ግን የተረጋገጠ ነገር ነው። ከምርጫ 2007 ወያኔዎች አሸነፍን እንደሚሉ ተረጋግጦ እንደነበረው፣ አቶ ይልቃል ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ሰማያዊን የምመራው እኔ ነኝ ብሎ ይመጣል።
መድረክ በቅርቡ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ብዙዎችን አሳዝኗል። ዉህደት የመፍጠሩን ነገር ሳይወስን፣ የጎሳ ድርጅቶች ስብስብ ብቻ ሆነ ለመቀጠል የወሰነ ይመስላል። በመድረክ ዉስጥ እንዳይቀጥሉም ለአንድነቶች በሩ የተዘጋባቸው ይመስላል።
አንድነቶች በመድረክ ሥር ለመቀጠል ከፈለጉ የኦፌኮ፣ ወይንም የአረና ወይንም የሲዳማ ንቅናቄ፣ ወይንም የደቡብ ድርጅት ወዘተረፈ አባል መሆን አለባቸው ማለት ነው። ለምሳሌ ኦሮሞ ያልሆነ፣ ትግሬ ያልሆነ ፣ የደቡብ ሰው ያልሆነ፣ ወይንም ኦሮሞ ትግሬ የደቡብ ሰው ሆኖ በዘሩ ሳይሆነ በኢትዮጵያዊነቱ መታገል የሚፈልግ ታጋይ እንዴት አደረጎ ነው የመድረክ አካል ሆኖ ሊሰራ የሚችለው ? ስለዚህ ለአብዛኛው የአንድነት የለዉጥ ሃይል በመድረክ ዉስጥ ሆኖ የመስራቱ ነገር ሙሉ ለሙሉ ተዘግቶበታል ማለት ይቻላል። መድረኮች ሌላውን ማቀፉ ሳይሆን ሌላው ማግለሉን የመረጡ ይመስላል።
ታዲያ የአንድነት የልውጥ ኃይሎች ፣ መቼም ዝም ብለው አይቀመጡም። ተደራጅተው መታገላቸው አይቀርም። እንዴት ነው የሚቀጥሉት ወደፊት የምናየው ይሆናል።

Friday, August 14, 2015

አለቃዎ ሳይሆን ቅን ህሊናዎ የሚያዝዎትን በመፈፀም መልካም ዜጋ ይሁኑ!

ginbot 7ይህን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ መጻሕፍት መፃፍ ይቻላል፤ መሠረተ ሀሳቡን ግን በጥቂት ዓረፍተ ነገሮች ማቅረብ ይቻላል።
መልካም ዜጋ ኢፍትሃዊ ተግባር ሲፈፀም “እኔ ምናገባኝ?” አይልም። መልካም ዜጋ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ”፤ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶም አይብቀል”፤ “እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም” እና በርካታ መሰል ምሳሌዎችን አይሰማም። መልካም ዜጋ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ከነፃና ቅን ህሊናው ጋር ታርቆ ይኖራል።
የህወሓት አገዛዝ፣ መልካም ዜጋ ማለት የመንግሥት ሥልጣን የያዘን ማንኛውም አካል ማክበርና በታማኝነት ማገልገል ተደርጎ እንዲተረጎምለት ይሻል። ፍትህ የሚያዛባ መንግሥትን መቃወም የመልካም ዜጋ አቢይ ተግባር መሆኑ የዘመናችን ወጣት እንዳይገነዘብ ያደርጋል። በተለይ ባለሙያዎች የሚያገለግሉትን አገዛዝ ባህርይ እግምት ውስጥ ሳያስገቡ የተቀጠሩበትን ሥርዓት በታማኝነት ማገልገል የዜግነት ግዴታቸው አድርገው እንዲወስዱት ይወተውታል።
ኦስካር ግሮኒንግ ( Oskar Groening)የዘጠና አራት ዓመት ሽማግሌ ጀርመናዊ ነው። በጀርመን የሂትለር አገዛዝ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን የተፈጁበት አሽዊትስ ካምፕ ውስጥ የሂሳብና ጽህፈት ሠራተኛ ነበር። ኦስካር ግሮኒንግ አንድም ሰው አልገደለም፤ አንድም ሰው አልገረፈም። እሱ ሂሳብ ነው የሠራው። ሆኖም በደል ሲፈፀም አይቶ “ምናገባኝ” ብሎ አልፏልና ከብዙ ዓመታት በኋላ ተከሶ በቅርቡ የ4 ዓመታት እስር ተፈርዶበት በሁለት እግሮቹ መቆም በማይችልበት በ 94 ዓመቱ በእርጅናውና በመጦሪያው ዘመን ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ፊት ተዋርዶ እስር ቤት ወርዷል።
በአንፃሩ ኦስካር ሽንድለር (Oskar Schindler) በጀርመን ናዚ ወቅት ሂትለር ይመራው የነበረው የናዚ ፓርቲ አባልና ሰላይ ነበር። ሆኖም ግን የሥርዓቱን ኢሰብዓዊነት ሲረዳ እዚያው የናዚ ፓርቲ ውስጥ ሆኖ አለቆቹ ያዘዙትን ሳይሆን ቅን ህሊናው ያዘዘውን በምስጢር መሥራት ጀመረ፤ በዚህም የ 1200 ሰዎችን ሕይወት ታደገ። ከጦርነቱ በኋላ ኦስካር ተከብሮ የኖረ በርካታ የክብር ስሞችና ሽልማቶች የተሰጠው በመልካም አርዓያነቱ የሚጠቀስ ሰው ሆነ።
በአገራችንም በአምስት ዓመታቱ የፋሽስት ወረራ ወቅት ስመ ጥር የውስጥ አርበኞች ነበሩ። ከነፃነት በኋላ ባንዶች እንኳን በውስጥ አርበኝነት ለመጠራት ያደርጉት የነበረውን እሽቅድድም ልብ በሉ።
በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴግ፣ ደህዴግ እንዲሁም አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ ያላችሁ ወገኞች ኦስካር ግሮኒንግን ወይንስ ኦስካር ሽንድለርን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ነገ የምትዋረዱበትን ሥራ መሥራት ነው የሚበጃችሁ ወይስ ዛሬ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ እየኖራችሁ ነገ ደግሞ ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ የሚኮሩበትን ተግባር መፈፀም ትፈልጋላችሁ? በአገዛዙ የስለላ ድርጅቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች ስማችሁን በመልካም ማስጠራት አትሹምን?
ልቦና ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! መልካም ዜግነት ሎሌነት አይደለም። መልካም ዜግነት ለቅን ህሊና ታማኝ መሆን ነው። መልካም ዜግነት ሲመች በገሀድ፤ ሳይመች በምስጢር ኢፍትሃዊነትን መዋጋት ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም መንገድ በአገዛዙ የፓለቲካ፣ የጦርና የፓሊስ ተቋማት፤ በስለላም ይሁን በሌላ የሲቪል ሙያ የተሰማራችሁ ወገኖቻችን የታዘዛችሁትን ሳይሆን ቅን ህሊናችሁ የሚጠይቃችሁን በመሥራት ኢፍትሃዊ፣ ፋሽስታዊና ዘረኛ የሆነውን የህወሓት አገዛዝን እንድታዳክሙ ጥሪ ያቀርብላችኋል። በአገዛዙ ውስጥ ሆናችሁ እያለም የምትሠሩት ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም በርካታ ሥራ አለ። የአገዛዙን ምስጢራዊ ሰነዶች ለአርበኞች ግንቦት 7 እንዲደርስ ማድረግ፤ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ፌስ ቡክና ቱተር) ማሰራጨት ትልቅ ዋጋ ያለ ሥራ ነው። የህወሓት ፀረ-አገር እና ፀረ-ሕዝብ ፕሮጀክቶችን ማሰናከል ሌላ ትልቅ ሥራ ነው። በነፃነት ታጋዮች ላይ የሚደረጉ ዱለታዎችን ማክሸፍ ሕይወት አድን ሥራ ነው። ድርጅቶቹ ውስጥ ሆኖ ድርጅቶቹን ማዳከም የመልካም ዜግነት ግዴታ መወጣት ነው።
በሥርዓቱ ውስጥ ሆነው ኢፍትሃዊነትን ለማጋለጥ እና ሥርዓቱን ለማዳከም ለሚጥሩ ወገኞች አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ክብር አለው፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅም የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ ሰው የሆነውን የህወሓትን ሥርዓት ለመጣል እና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና የሀገር አንድነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለማጽናት ከሥርዓቱ ውስጥም ውጭም የሚደረገውን ትግል እናፋፍም።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7

የክረምት ዝናብ ዘግይቶ መጀመሩ አሳሳቢ ሆኗል፤ በአፋርና ኢሳ አካባቢዎች ለ5ወራት የዝናብ እጥረት ተከስቷል -

4835A12F-B64D-49D7-BB4D-886F3E204E6A_w640_r1_sበኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ በእጅጉ ዘግይቶ በመጀመሩ፤ በከብት እርባታ የሚተዳደሩ የአፋርና ኢሳ አካባቢዎች መጎዳታቸውን የማህበረሰቦቹ ተወካዮች ገለጹ።
በድርቁ የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች  የሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካታ እንስሳት መሞታቸውን፤  የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከአፋርና ኢሳ ማህበረሰቦች መሪዎች ካገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
የፌዴራልና የክልል ባለስልጣንት በአንዳንድ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የከብት መኖ ማቅረብ መጀመራቸውን ለመረዳት ተችሏል። ስርጭቱ ግን አሁንም በስፋት በድርቁ የተጠቁ አካባቢዎች ያዳረሰ አይደለም።
የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በዘንድሮው ክረምት ባብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት መከሰቱን ሰኞለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህንኑ መነሻ በማድረግም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ኮሚቴ መቋቋሙ ተገልጿል። የዝናቡ እጥረት በሰዎችና በእንስሳት ላይ ያደረሰው ጉዳት ስለመኖሩ መንግሥት እስካሁን ባለው ጊዜ የሰጠው ዝርዝር መግለጫ የለም።
ያሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ያነጋገራቸው የአፋርና የኢሣ ማህበረሰብ መሪዎች ግን ሰዎችና በርካታ ከብቶች መሞታቸውን ገልጸው የክልልና የፌዴራል መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ተማጽነዋል።

Monday, August 10, 2015

“በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ” – ትህዴን -

arbegnoch ginbot 7መስዋእትነት አይቀሬ ነው ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ግን ክብር ነው!! የትህዴን ርዕሠ አንቀጽ በአሁኑ ግዜ በአገራችን ህዝብን የሚወክልና በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይኖረን ይህንን እድል ለመፍጠር አጋጣሚውን ያገኙ ቡድኖች ሆኑ ግለሰቦች ከህዝብ ፍላጎት እና ከሃገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን‘ና የባእዳኖችን ፍላጎት በማስቀደም ያገኙትን የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የህዝብን ስልጣን እየነጠቁ ለህዝብ እና ለሃገር የቆሙትን እየገፉ እና እየገደሉ በጉልበት መንግስት ነን በማለት እስካሁን ስልጣን ላይ ይገኛሉ። የኢህአዴግ አመራሮች ህዝብን የማገልገል ስራ ሳይሆን የየራሳቸውን ጥቅም በማስጠበቅ እና ስልጣን ላይ ወጥተው የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ፤ ህዝብን እንዳሻቸው እየጨቆኑ፤ እያንገላቱና እየጨፈጨፉ ባጠቃላይ ለትውልድ የሚተርፍ መጥፎ ታሪክና የማይረሳ የጥፋት አሻራ ጥለው እያለፉ መሆናቸው ግልፅ ነው። የደርግ ስርዓት በህዝብ ልጆች መስዋእትነትና የአካል-መጉደል ከተደመሰሰ በኃላ ስልጣን የሙጥኝ ያለው ፀረ ህዝብ የኢህአዴግ ስርዓት ፋሺስታዊው የደርግ ስርዓት ለሃገር እና ለህዝብ የቆሙትን ንፁኃን ዜጎች በመጨፍጨፍ እንደሚታወቀው ሁሉ አሁን በአገዛዝ ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓትም በፖለቲካ አመለካከታቸውና ደስ አላሰኙኝም በሚል ንጽሁሃን ዜጎች በድብቅና በግልፅ ብመጥፋት የራሱ የሆነ ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሃገር የሆኑ መለያዎች አሉት። የኢህአዴግ ስርዓት ካለፉት ጨቋኝ ስርዓቶች ለየት የሚያደርጉት በርካታ እኩይ ባህሪያቶች እዳሉት ግልጽ ነው። ስርአቱ የሚታወቅበት መቼም ሊለወጥ እና ሊሻሻል የማይችል አያሌ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ አጀንዳዎች እንዳሉ ሆነው በተጨማሪም አለቆቹ በባእዳን የተነገረውን ትእዛዝ ለማስከበር ሲሉ ለባእዳኖች ባለመገዛቱ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመበቀል፤ኢትዮጵያን ለመበታተን’ና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተዘጋጀውን የተሳሳተ ታሪክ ይዞ በተለይም ለስርዓቱ አልገዛም ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቂም ይዞ ለመበቀል ከፍተኛ በጀት እና የሰው ሃይል መድቦ ለጥፋት መነሳቱ የስርዓቱ ባህሪ ነው። እንደሚታወቀው በመሳሪያ ጋጋታ እና በአፋኝ ህግ ብዛት ሃሳቡን እና ተቃውሞውን እንዳይገልጽ የተከለከለው የኢትዮጵያ ህዝብ ለስርዓቱ ያለውን እምቢተኝነት እና ተቃውሞ ባገኘው አጋጣሚ እየገለጸና ከዛም አልፎ የስርዓቱ አስመሳይ የምርጫ ሂደት ላይ ባለመሳተፍና ባለመምረጥ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጿል። በመሆኑም የኢህአዴ ስርዓት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በስልጣን መቆየቱ የቂሙን ደረጃ የት ያደርሰዋል? ስልጣኑንስ የሚጠቀመው እውነት ሃገር እና ህዝብን ለመጥቀም ነው? ወይስ የተነሳለትን ኢትዮጵያን ህዝቧን የመበታተን ዘመቻውን አጠናክሮ ለማስቀጠል? ለማኛውም! አጥፊ እና ጠፊ አብረው መኖር እንደማይችሉ ሁሉ መቼም ቢሆን ህዝብ ከኢህአዴግ ስርዓት ጎን ሊቆም አይችልምና ህዝቡ ለኢህአዴግ ባለመምረጡና ከህወሓት-ኢህአዴግ ጎን ባለመቆሙ ምክንያት የተለመደ የኢህአዴግ ቂም በቀል እርምጃ በእጥፍ መቀበሉ አይቀሬ ነው፤ ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው የጥፋት ዘመቻ፤ እስራት፤ ድብደባ፤ አፈና፤ በኑሮ ውድነት መሰቃየት፤ ከኖረበት መፈናቀሉ ሌላም ሌላም በከፋ ሁኔታ ይቀጥላል። በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ምክንያቱ የእኛ ከኢትዮጵያውያን ታሪክ አንጻር ሲታይ ለውጭ ወራሪውችም ሆነ ለውጥ ጸረ ህዝብ ስርአተወች አሜን ብሎ ተገዝቶ ኣይውቅም ስለዚህ መቼም ቢሆን አይቶ እንዳላየ መሞትን ይመርጣል ተብሎ አይገመትም። ስለሆነም ማንኛው ኢትዮጵያዊ በሚከተለው ዓላማና በፖለቲካ አስተሳሰቡ ህይወት መክፈሉ ላይቀር እራሱን መስዋእት አድርጎ ብሄራዊ ክብሩን ለማስመለስና በሃገራችን ውስጥ እውነተኛና ያልተገደበ ዴሞክራሲ ለመገንባት፤ ለህዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ የሆነ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ለመመስረት በሚደረገው ትግል ላይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል፣ ምክንያቱም ለማይቀረው መስዋእትነት ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ክብርን ያጎናፅፋልና።

Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም

Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም -Habitamuየህብር ሬዲዮ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ፕሮግራም
<...መድረክ በዚህ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔው በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።የገዢው ፓርቲ መጠቀሚያ ምርጫ ቦርድ ፈርሶ ገለልተኛ ቦርድ እንዲቋቋም፣ ሁሉንም የሰላማዊ የትግል ስልቶች ተግባራዊ የሚያደርግ የተጠናከረ ትግል ለማድረግ ይንቀሳቀሳል፣ እውነተኛ ተቃዋሚዎች ወደ ቅንጅት፣ግንባር ከተቻለ ወደ ውህደት እንዲመጡ ጥሪ አድርጓል፣ ለድርቁ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል ... የህወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ውጥረት ተሸጋግሯል መቀሌ ላይ ልዩ ሀይል በጥበቃ ላይ ነው። የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች የሁለቱ የአዲስ አበባና የመቀሌ ቡድኖች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ትቃት ይቀየራል የሚል ስጋት አላቸው። ህዝቡ ግን የሚያሳስበው ዝናብ ስለሌለ ድርቁ ነው…>
አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የመድረክን ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እና የህወሃት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<...አንዱ ወንድሜ ግንቦት ሰባትን ወደ በረሃ ሄዶ በመቀላቀሉ ከፖሊስ ጣቢያ ከመሸ በሁዋላ ወስደው ከፍተኛ ማሰቃየት ፈጽመውብኛል።በደረሰብኝ ድብደባ ስዳከም ከመሀከላቸው አንዱ ወጥቶ እየደከመ ስለሆነ ሆስፒታል ሲመጣ የሞተው ተደብድቦ ነው እንዳይሉ ብሎ ደውሎ ስሜን ሲሰጥ በሰመመን ውስጥ ሰማሁ …> ወጣት ባንተወሰን አበበ በአርባ ምንጭ ከተማ ወንድሙ ግንኦት ሰባትን ለትግል በመቀላቀሉ ሳቢያ በደህነቶች የደረሰበትን ስቃይ ለህብር ሬዲዮ ገልጿል ( ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ፕሬዝዳንት ኦባማን ለመግደል የአልሸባብ ህዋስ ሆነህ ተንቀሳቅሰሃል ሲሉ ነው ሊከሱኝ የሞከሩት።በጨለማ ከሌሎቱ አምስት ሰዓት ከሀያ በላይ ፖሊሶች መጥተው ተይዤ ነው የተወሰድኩት ። በሌሊት ተወስጄ በሌሊት ተፈትቼያለሁ ። አሁንም አብረኸን ካልሰራህ የማትወጣው ችግር ውስጥ ትገባለህ ብለውኛል። …> ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ አስገራሚ ስለሆነው የተለጠፈበት ወንጀል እና የእስር ቆይታው ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የሚድትራኔያን ባህርን አቋረጠው ከፈረንሳዩ የካሌስ ወደብ የደረሱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዛሬም ያነባሉ(ልዩ እና ወቅታዊ ዘገባ)
ለኢትዮጵያውያን ቀን በቬጋስ የበዓል አከባበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሪፖርት
ከሁበር መምጣት በፊት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቃለ መጠይቅ
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
የሕውሃት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊሸጋገር ይችላል ተባለ
መድረክ በልዩ ጉባዔ አገዛዙ የግብዣ ጋጋታውን ትቶ በድርቅ እየተጎዳ ላለው ህዝብ እንዲደርስ ጠየቀ
የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሴናተሮች አቶ አንዳርጋቸው ባሰቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ
ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ወጣት አበሻ ሰደተኞችን በማሰጠለላቸው የግደያ ዛቻ ገጠማቸው
ከ700 በላይ ሰደተኞችን ከሊቢያ ወደ ጣለያን የጫነች ጀልባ አስዛኝ የሆነ አደጋ ገጠማት
እስራኤል ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በልዪ የሆድ እቃ ህመም እየተስቃዩ ናቸው ተባለ
የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በማዕካዊ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለመታወቁ ተገለፀ
የኔቫዳ የትራንስፖርት ባለስልጣን ሁበርና ሊፍት ላይ ጫና ይፈጥራል የተባለ ረቂቅ ደንብ አቀረበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45753#sthash.B4xyH5re.dpuf

Friday, August 7, 2015

አራቱ የበረከት ስምዖን እንግዶች (ጥብቅ ምስጢር – ያንብቡ)

simonጥር 6 ቀን 2002 ዓም በተለምዶ ጉበት ከለር እየተባለ የሚጠራውን ቀለም የተቀባች ኮድ ሁለት የታርጋ ቁጥሯ 63795 የሆነች ‹‹ ወያኔ›› ዲኤክስ የቤት አውቶሞቢል ሾፌሩን ጨምሮ አራት ሰዎችን ይዛ ወደ ኢህአዴግ ፅ/ቤት እየከነፈች ነው ሾፌሯ የመኪናዋ ባለቤት ነው ፡፡ሶስት እንግዶችን ባስቸኳይ አቶ በረከት ቢሮ እንዲያደርስ ነው የታዘዘው ሁለት ወጣቶችንና አንድ ሰውነቷ ሞላ ያለች ሴትይዟል ፤የካቴድራል ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን በር ሊደርሱ ጥቂት ሲቀር የግንብ አጥሩ ከቤተክርስቲያኑ ግምብ ጋር የተያያዘው ግዙፉ የኢህአዴግ ፅ/ቤት በር ላይ ቆሙ እጆቻቸውን ከመሳሪያቸው ምላጭ ላይ ከማይነቅሉት ላብ አደር የመከላከያ ሠራዊት መካከል አንዱ ጠጋ አለና ‹‹አቤት ›› አለ ከሾፌሩ አጠገብ የተቀመጠችው ሴት ወ/ሮ ‹‹ አቶ በረከት ጋር ቀጠሮ አለን ›› አለችው ወታደሩም ‹‹ሁላችሁም›› አለ ‹‹ አዎ ›› አለች ራመድ አለና ከአንድ ሌላ የእሱ ቢጤ ጋር ተነጋግሮ በሩ ስር ካለች አነስተኛ ቤት ወረቀት ይዞ ወጣና አነበበ ወደ መኪናዋም ተጠጋና የአራቱንም መታወቂያ ጠየቀ ተሰጠው በስማቸው ትክክል ከመታወቂያቸው ላይ ካመሳከረ በኋላ በባለ ዘንግ ክብ መስተዋት የመኪናዋ ሆድ እቃ ሳይቀር ተፈትሽው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደላቸው ወታደሩ ይዟት መጥቶ የነበረው ወረቀት ‹‹ ወ/ሮ ሙሉ ከነመኪናቸው ይግቡ›› የሚል ከበረከት ስምዖን ቢሮ የተላከች የመግቢያ ፈቃድ ነበረች ፡፡
አራቱም ሰዎች ከበረከት ፀሐፊ ከዓለም ጠረቤዛ ደረሱ በሃይላንድ ውሃ ጉዳይ ከህላዌ ዮሴፍ ጋር እየተጨቃጨቀች ነበር ቀልደኛውና ሲፈጥረው ባለስልጣን መሆን ያልነበረበት ህላዌ አይቷቸው የማያውቀውን አንግዶች ሲያይ ደንገጥ አለና ወደ ኋላው ሁለት ርምጃ ተሳበ አንግዶቹ አለምን እየጨበጡ መግባት ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ በወቅቱ የስምዖን ልጅ በረከት ከአዲሱ ለገሰ ጋር ውይይት ላይ ስለነበር ‹‹ ቁጭ በሉ ከሰዓታችሁ 20 ደቂቃ ቀድማችኋል አለቻቸው›› ተቀመጡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አዲሱ እየሳቀ ከበረከት ቢሮ ሲወጣ እሱም አንግዶቹን አየና አልፏቸው ሊሄድ ብሎ መለስ አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላቸው በአክብሮት ጨበጡት ወ/ሮዋን ሲጨብጥ ጠበቅ አድርጎ ያዛትና ‹‹የት ነው የማውቅሽ ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ነው አራተኛ ነው … እዚህ ቦታ እዚያ ቦታ ››እያለ ሲያስጨንቃት ወ/ሮዋ ፈገግ በማለት ብቻ ዝም አለችው አዲሱ ግን ተሸውዷል በወቅት ወ/ሮ ሙሉን የትም ቦታ አያውቃትም ነበር፡፡
በረከት ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበላቸው ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሾፌሩ ወደ ውጪ ወጣና ፀሐፊዋ ዓለም ጋር የመጣለትን ወፍራም ቡና እየጠጣ ከፊት ለፊቱ ‹‹ልማታዊውን ባለሀብት አትንኩት›› የሚል ትዕዛዝ ይሁን ልመና ፁሁፍ ያለበትን የሼክ አላሙዲንን ፎቶ እያየ በሀሳብ ሄዷል ሶስቱ ሰዎች ረዘም ላለ ሰዓት ቆዩ ድንገት ያልታሰበ ነገር ተከሰተ የታላቁ ባለስልጣን የአቶ በረከት ቢሮ በኃይል ተበረገደና ወ/ሮዋ ስትቀር ሁለቱ ወጣቶች በቁጣ መንፈስ ወጡ በዚህ ጊዜ ጸሀፊዋ ዓለም በፍጥነት ተነስታ የበረከትን ቢሮ እንደመዝጋት ደህንቱን እንደማረጋገጥም ወደ ውስጥ አየት አድረጋ መልሳ ዘጋችው ሁለቱ በፍጥነት ደረጃውን እየወረዱ ነበር ከጥቂት ቆይታ በኋላም ወ/ሮዋ ወጣች በር ላይ ቆሟ ግን አንዲት ቃል ወረወረች ‹‹በረከት ግን ጊዜ ወስደህ አስብበት ይህ ለሁላችንም (ለማንም) አይበጅም አለችው ተጨማሪ ንግግር ልታደረግ ያሰበች ትመስል ነበር ግን ከአፍንጫው ከፍ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ንቅሳት ያለው የበረከት ስምዖን የግል ጠባቂ ከዚህ መጣ ሳይባል ድንገት ከተፍ ብሎ ወ/ሮዋን እንደ ማባበልም እንደ መግፋትም አድርጎ ቢሮውን ከጀርባው እየዘጋ ደጋግፎ ሸኛት ፡፡
በወቅቱ በረከት ቢሮ የመጡት እነዛ ሰዎች እነማን ናቸው ? የተነጋገሩትስ ሰለምንድን ነው? ያልተግባቡትስ በምንድን ነው ? ይህን ጉዳይ ከእኔ ከፀሐፊዋ ይልቅ የአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ አሳምሮ ያውቀዋል:: ፁሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት እነዛ አራት ሰዎች አሁን የት ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ልስጥ የመኪናዋ ባለቤትና ሾፌር የነበረው በአሁን ወቅት ከኢ/ር ዘለቀ ረዲ ጋር በገጠር መንገድ ሥራና በታላላቅ የውሃ ቁፋሮ ሥራ ተሰማርቶ ሚሊየነር ሆኗል:: አንደኛው ገጣሚ ሙሉ ሰሎሞን ራት ጋብዛው ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ከካዛንቺስ ወደ መገናኛ መኪናውን እያሽከረከረ ሲሄድ በተሳሳተ መንገድ ከሌላ አቅጣጫ በሚመጣ መኪና ይገጭና ይቆማል:: ድንጋጤው አልፎለት ከመኪናው ሊወርድ ሲል በገጪው መኪና ውስጥ ከነበሩ ሰዎች በተተኮስ ሽጉጥ ተገደለ:: ሶስተኛው ሰው በአሁን ወቅት ወሊሶ ወህኒ ቤት የማያውቀው ወንጀል ተለጥፎለት የሰባት ዓመት ፍርደኛ ሆኖ ተኝቷል:: አራተኛዋና ወ/ሮ ሙሉ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ በሚሊየን የሚቆጥር ገንዘብ አጭበርብራለች ተብላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነችና ነነዊት አፈወርቅ ከተባለች ልጇ ጋር 28 (ሃያ ስምንት) ዓመታት ተፈርዶባት ቃሊቲ ተጥላለች፡
እስኪ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ወ/ሮ ሙሉ ኃይለማርያም በምን እንደተሳረች የዘገቡትን አድምጡና ፍርድ ስጡ ምን ያህሉ ተዓማኒ ነበር ?እኚህ ስማቸውን መግለፅ አንፈልግም የተባሉና የተጠየቁትን ሚሊዮኖች እያወጡ የሚሰጡ ሰው ማናቸው? ሊንኩን ተጭነው ዜናውን ያድምጡ

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45658#sthash.7CmJ42bV.dpuf

ኤፍሬም ማዴቦ የሞቀውን ኑሮውንና ቤተሰቦቹን ትቶ ወደ ኤርትራ አቀና –

Ephrem Madeboሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊሰማው የሚገባ ኤፍሬም ማዴቦ – ” የኔ መሞት ለኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት ከሆነው ህይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ” እንዳለው አልቀረም የሞቀውን ኑሮውንና ቤተሰቦቹን ትቶ ወደ ኤርትራ አቀና

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ

_አሜሪካ ከ25 ዓመት በፊት በስደት ገቡ።
_በአሜሪካ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታተሉ።
_ከታዋቂው ጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርስቲ በማዕረግ ተመረቁ።
_በኢኮኖሚክስ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
_በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በተመሳሳይ ላቅ ያለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
_በአሜሪካን ፌደራል መስሪያ ቤት ከፍተኛ ደምወዝ ከሚከፈላቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ናቸው።
_በተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ከአባልነት እስከ አመራርነት አገልግለዋል።
_የቤተሰብ ሃላፊና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመሩትን የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር በመቀላቀል ከትላንት በስቲያ ኤርትራ ገብተዋል።

Thursday, August 6, 2015

‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› – ሐና ሙሉጌታ

Eriteriaበአንዲት ጎደሎ ቀን ም/ፕሬዝደንቱን ጨምሮ አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኤርትሪያ ይበጃታል ያሉትን አንድ ቀና ነገር አሰቡ፤ ሃሳባቸውም ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ከስልጣናቸው በፈቃዳቸው እንዲለቅቁ አድርገው በምትካቸው ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሊቀላቅላቸው የሚችል ትንሽ ትምህርት ቀመስ የሆነ ሰው በስልጣን ላይ ማስቀመጥ የሚል ነበር ይህንንም እቅድ ውስጥ ውስጡን ሲያበስሉት ቆዩና በመግቢያዬ እንደገለፅኩት በአንዲት ጎደሎ ቀን በኮድ ስሟ ‹‹ 011 ›› በተባለች አዳራሽ ተሰብስበው ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ይጠብቃሉ ሰዓቱ 21 ፡00 ሲል ፕሬዝደንቱ ወደ አዳራሹ ገቡ ገና መቀመጫቸው ወንበሩን ከመንካቱ ጥቂት ምስጢራዊ ሰዎች ብቻ የሚያውቋት ስልካቸው ተንጫረረች አነሷት የተደወለው ከሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ከአብረሃ ካሳ ነበር ስልካቸውን ወደ ጆሮአቸው አስጠጉ ‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› የሚል መልእክት ሰሙ ፤ ፊታቸው አመድ መሰለ በቀስታ ዘወር ብለው በአዳራሹ የተሰበሰቡትን አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በዓይናቸው ቃኟቸው ሠላሳ ዓይኖች አፍጥጠውባቸዋል፤ ሹልክ ብለው በመጡበት እግራቸው አዳራሹን ለቀው ወጡ ፡፡

እነዚያ ለኤርትሪያ ሲሉ ስንት መስዋዕትነት የከፈሉ አንቱ የተባሉ ባለስልጣናት እጅና እግራቸው በካቴና ተጠፍንገው ጨለማ ቤት ተወረወሩ ታዲያ ያኔ መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉብህ ነው ብለው አስራ አምስት ፊደላትን ብቻ በፕሬዝደንቱ ጆሮ አሰምተው አስራ አምስቱን ባለስልጣናት ያስበሉ የፀጥታው መ/ቤት ሹም አብረሃ ካሳ ዛሬ የወያኔ ሰላይ ሆነው በውል የተረጋገጠ 1. አዲስ አባባ ላይ ባለ አስር ፎቅ ህንጻ ፣ 2. ጋምቤላ ሰፊ እርሻ ፣ 3. አፍዴራ የጨው ማምረቻ እንዲሁም 4. አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ጀርባ ቋሚ ነዋሪነቱን ሱዳን ካደረገ ነቢል አልቁሙስ (አል-ኩሙስ) ከተባለ ግብፃዊ ጋር በሽርክና ዓለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅት በወንድማቸው ስም ከፍተው ቢዝነሱ ውስጥ ሲጨማለቁበት በምላሹም ወያኔዎች የኤርትሪያን ፣የግንቦት ሰባትን የአርበኞች ግንባርን መረጃዎች አንድ በአንድ ሲዘረግፉ ኖረው ተደርሶባቸው በተራቸው ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸዋል በዚህ ሁኔታም የኤርትሪያ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ዛሬ 8/5/2015 ነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከግለሰቡ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የግለሰቡ ዘመዶችም ተጠቃለው በየማጎሪያው ገብተዋል በመጨረሻም አቶ ኢሳይያስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል ‹‹ ግድ የለም እናንተ ሆዳችሁን አስፉ እኛ ደግሞ አዲኳላን እናሰፋለን ›› አዲኳላ ምን ይሆን ?

ለሁለት የተከፈሉት ህወሀቶች በከባድ ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸው ተሰማ

11828814_889695077788816_1098721813211188712_nየህወሓት ሁለቱ ኣንጃዎች ፍጥጫ…!
ህወሓት የሚመራው መንግስት በትግራይ ህዝብ፣ ሙሁራን፣ ተማሪዎች፣ የፖለቲካ ኣክቲቪስቶች፣ የህወሓት ኣባሎች ሳይቀሩ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰው ይገኛል።
ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ ህወሓት የነበረት ግርማ ሞገስ ያጥች ስትሆን በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት የተከፈለችው ህወሓት ጠበንጃዋ ኣንግባ ሁሉንም የተለየ ሃሳብ የያዘ ሰው የተለያዩ ቅጥያ እያሰጠች ድራሹን ስታጠፋው ነበር።
የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር የነበረው ቁርኝት ከፍተኛ ከመኖሩና ሙሉ ድጋፍ እንደሰጣት ዋና ማሳያው “ውድብና”( ድርጅታችን ) ሲላት ለታጋዮችም “ደቅና”(ልጆቻችን) በሚል የማቆላመጥ ስም ይጠራት ነበር።
የህወሓት ጥፋቶች በስራ የሚከሰቱ ስህተቶች በመቁጠር ይቅር እያለ እያለፈ ከነ ችግሮቿ ተሸክሞ ዓመታት ቢጠብቅም በረኻ እያለች የገባችለት ቃል ክዳ ለጥቂት ባለ ስልጣኖች ብቻ የቆመች መኻንና የህዝቡን ችግር፣ ፍላጎትና መስዋእትነት የማይታያት ዓይነ ስውር መሆንዋ ማረጋገጥ ከጀመረ በሗላ የትግራይ ህዝብ “ውድብና” ሲላት የነበርችው በስሟ “ሕወሓት” ብሎ መጥራት “ደቅና” (ልጆቻችን ) የሚለውን “ንሳቶም”(እነሱ)ብሎ መጥራት ከጀመረ ዓመታት ኣልፈዋል።
ህወሓት የህዝብ ጥያቄ፣ ችግር፣ እሮሮ፣ ስቃይ፣ እርዛት፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች መስማት የማትችል ዱዳ ሁና ኣልፈዋለች።
የትግራይ ህዝብ የህወሓት ስም መጥራት ተጠይፎ “እነሱ” እያለ ቢጠራቸውም ኣመራሮቹም ሰሚ ጆሮ ኣልነበረባቸውም።
የትግራይ ህዝብ ህወሓት “ጠላቶችህ ሊውጡህ ኣሰፍስፈው እየመጡ ነው፣ እኔ ከሌለው ኣንተ መጥፋትህ ነው” የሚል ፕሮፖጋንዳ ብቸኛው የድጋፍ ምንጭ ኣድርጋ ስትጠቀምበት የነበረችው ከንቱ መቅረት የጀመረውና ህዝቡ የራስ መተማመኑ መመለስ የጀመረው ዓረና ትግራይ ከተመሰረተና በመላ ትግራይ ተንቀሳቅሶ ህወሓትን የሚያስንቅ ፖለቲካዊ ኣቋምና ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ለትግራይ ህዝብ ሊያጠፋ የሚያስብም የሚችልም እንደሌለ በማረጋገጡ፣ ለዘመናት ድህነት፣ ሙስና፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦት፣ በኣገሩ እኩል የመጠቀም መበትና ሌሎች ዲሞክራሲያዊና ሰብኣዊ መብቶች ሊከበሩለት የሚያስችል የተሻለ ኣማራጭ ይዞ ሲመጣ ከፍተኛ ድጋፉን ሰጥተዋል።
ህወሓት በኣጭር ግዜ ዓረና ያገኘው ህዝባዊ ቅቡልነት መርምሮ ለማስተካከልና ያጣውን ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ከማስመለስ ይልቅ ዓረና ድርጅት ለማፍረስ ሰርጎ ገቦች ማሰማራትና በዓረና ኣባላት ላይ እስከ ግድያ የደረሰ ጥቃቶች ስትፈፅም ግዜዋን ኣሳልፋዋለች።
እነዚህ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ተግባሮች በዓረና ኣባላትና በትግራይ ህዝብ ዘንድ የታዩት ህወሓት በሌላ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መቀያር ያለባት መሆንዋ ራስዋ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ሁነው ጠቅመዋል።
የዘንድሮ 2007 ምርጫ የህወሓት ህዝባዊ መሰረት ከስሩ የተነቀለበትና በስልጣን የመቆየትዋ ምክንያት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠበንጃዋና ዓፈናዋ ብቻ መሆኑ ፍንትው ኣድርጎ ኣሳይቶን ኣልፈዋል።
የ”100 ፐርሰንት” ድምፅ ልፈፋ በመሬት የሌለ መሆኑ የኢትዮዽያና የትግራይ ህዝብ፣ የተቃዋሞ ድርጅቶችና ኣባሎቻቸው፣ የተቀዋሚ ደጋፊዎች፣ የገዢው ፓርቲ ኣመራሮች(ምርጫው ካለፈ ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ የትግራይ ካድሬ ሰብስበው ኣዋርዳቹናል በሚል ዘለፋና ስድብ ኣዝንቦባቸው ነበር) ፣ ኣባላትና ደጋፊዎች ሳያወላውሉ ያረጋገጡበት ዕድል ፈጥሮ ኣልፈዋል።
የምርጫው ምጤትም
—————-
፩) የዓረና ኣባላትና ደጋፊዎች የዘንድሮ ምርጫ የትግራይ ህዝብ ተሳትፎና ለዓረና የነበረው ድጋፍ በጣም ኣስገራሚ ነበር። ህዝቡ የህወሓት ያማጥላላት ፕሮፖጋንዳ ሳያደናግረው በልበሙሉነት ዓረናን መርጠዋል። የዓረና ኣባላትና ደጋፊዎች በኣሁኑ ሰዓት የኣሸናፊነት መንፈስ የድል ኣድራጊነት ወኔ ተላብሰው የገኛሉ።
፪) የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ኣመራሮች፣ ኣባላት፣ ሙሁራንና ወጣት ኣባሎች ከፍተኛ የሽንፈት ስሜት አያንፀባረቁ ይገኛሉ። እነዚህ የህወሓት ኣባሎች በሁት የሚከፈሉ ሲሆኑ የኣዲስ ኣበባና የትግራይ ኣንጃዎች ተብለው ተባዱነዋል።
፫) የ”ልማታዊ ባለሃብቶች” ተብለው በህወሓት የተመደቡትና ህወሓት ፈጠርኳቸው ብሎ ዘወትር የሚዘምርላቸው ባለሃብቶችም በህወሓት ህልውናና የመቧደን ስራ ተጠምደው ይገኛሉ። እነዚህም የኣዲስ ኣበባና የትግራይ የሚል ስም ይዘዋል።
፬) ወጣትና ፊደል ቀመስ የህወሓት ኣባላትም እንደዚሁ የትግራይና የኣዲስ ኣበባ የሚል ቡዱን ሰርተው በየፊናቸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
፭) የትግራይ ወጣቶችም የህወሓት ኣቅመቢስነትና እንደ ህዝባዊ ድርጅት የመቀጠል እድሏ ኣጠራጣሪና እርባና ቢስ መሆኑ በመረዳት የተልያዩ መሰባሰቦችና ኣዲስ ፖለቲካዊ ድርጅት የመመስረት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ሙከራዎች እያደረጉ ይገኛሉ።
እነዚህ እንቅስቃሴዎች ህወሓት ኣሁን ባለችበት ደረጃ ሁና መቀጠል እንደማትችል ድምዳሜ የደረሱ ናቸው።
“በኣሁኑ ሰዓት ህወሓት በጥሩ ኣቋም ላይ ትገኛለች” የሚል ኣቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ክልል ቡድን ኣቶ ኣባይ ወልዱና ቴድሮስ ሓጎስ የሚመሩት ሲሆን የነዚህ ደጋፊ የሆነው የወጣቶች ቡድን “ስልጣኑ ለኛ ወጣቶች መሸጋገር ኣለበት” የሚል የኣዳሽ ኣቋም ይዞ የሚደግፋቸው ነው።
የነሓሴ ወር ጉባኤና የሁለቱ ኣንጃዎች ቅስቀሳ
————————————-
ህወሓት 12ኛው ጉባኤዋ በመቐለ ከተማ ነሓሴ 14/ 2007 ትጀምራለች።
በዚህ ጉባኤ ኣሸንፎ ለመውጣት የኣዲስ ኣበባና የትግራይ ኣንጃዎች የየራሳቸው ቅስቀሳዎች እያካሄዱ ይገኛሉ።
A) የትግራይ ቡዱን = ይህ ቡዱን “ትግራይ በጣም ኣድጋለች፣ ህዝባችን ከድህነት ተላቀዋል፣ 11 ፐርሰንት ኣድገናል፣ ሙስናና መልካም ኣስተዳደርም ጠላቶች(ዓረናና የኣዲስ ኣበባ ኣንጃ በኣንድነት የሚከስ ነው) እንደሚያወሩት ኣይደለም። መለስ የተወልን ራኢ ይዘን ለ50 ዓመት ኢትዮዽያን እንገዛለን” የሚል ሆኖ እንደ ዋነኛው ሃይል ኣድርጎ የሚንቀስቀሰውም
1) ከክልል እስከ ቀበሌ የተደራጀው ኣባልና ኣቶ ኣባይ ወልዱን ሊቀ መንበር ኣድርጎ ያስመረጠው ኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ(1ለ5) ኣደረጃጀት ተጠቅሞ የኣዲሳበባው ኣንጃ በጉባኤው ካድሬውን ተጠቅሞ ኣሽቀንጥሮ ለመጣል ነው። የዚህ ማሳያም በመላ ትግራይ ያሉት ኣደረጃጀቶች የጉባኤው ተሳታፊ ካደሬ መልምሎ “.የመለስ ራኢ እንዳትክዱ ድርጅታችንን እንዳትወድቅ ኣደራ” እያለ እያስማለቸው ይገኛል።
2) በትግራይ ክልል ያሉት ባለሃብቶች በተለይም ከባለስልጣኖች ተባብረው ሃብት ያጠራቀሙ ደጋፊዎቻቸው ኣደራጅተው የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ለማሸነፍ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
፫) የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ሁነው ከፍተኛ ሃብት መሰብሰብ የቻሉትን ጭምር ድጋፍ ለማግኘት እየሰሩ ናቸው።
B ) የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ= ይህ ቡድን “የመለስ ራኢ” የሚል ሽፋን ተከናንበን ትግራይ ውስጥ እየሰራን ያለነው ለድርጅታችን ህልውና ኣደጋ ላይ የሚጥል ነው” የሚል ኣቋም ያንፀባርቃል።
በትግራይ ክልል ድህነት ኣንሰራፍተዋል፣ ረሃብ፣ የመልካም ኣስተዳደር ችግር፣ የሙስና መስፋፋት፣ በኣጠቃላይ “የመለስ ራኢ” በሚል ሽፋን ተሽፍነን በዳታ ክምር ብቻ ድርጅታችን መቀጠል ኣትችልም።
ተቃዊሚዎች እያግኙት ያሉት የህዝብ ድጋፍም በያዙት ጠቃሚ ኣማራጭ ሳይሆን በኛ ድክመት ነው” የሚል ኣቋም ይዘው እየተታገሉ ነው።
ሀ) የነ ዶክተር ደብረፅዮንና ዶክተር ኣርከበ ዕቑባይ የሚመሩት ኣንጃ ሲሆን “ህወሓት ኣሁን ባለችበት መንገድ ከቀጠለች ለህልውናዋ ኣደጋ ነው።” የሚሉትና “ኣሁን ከቀበሌ እስከ ፖሊት ቢሮ ያለው ኣመራር ኣቅመ ቢስና በሙስና የተዘፈቀ መሰረታዊ የኣመራር ለውጥ ማምጣት ግድ የሚል ነው” ብሎ የሚያምን ነው።
ለ) የዚህ ኣንጃ ደጋፊዎች በትግራይ ክልል እንዳይሰሩ የተለያዩ እንቅፋቶች የደረሰባቸው ባለ ሃብቶች እና በተለያዩ ጫናዎች ተሰላችተው ከትግራይ የተሰደዱ ልማታዊ ባለሃብቶች ሲሆኑ እነዚህም የትግራዩ ኣንጃ ከተሸነፈ በትግራይ መስራት የሚፈልጉ ናቸው።(ኣቶ ኣባይ ወልዱ ወደ ኣስተዳዳሪነት በመጡበት ወቅት ከኣለማጣ እስከ ሑመራ እነ ገዛገርላሰና ኣርጋዊ ሃይሉ ጨምረው ከ110 በላይ ባለሃብቶች ማሰራቸው የሚታወስ ነው።)
ሰሞኑን ኣቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር በዓይጋ ፎረም በኩል የትግራይ ሁኔታና ያሉት ችግሮች ኣፍረጥርጠው የተናገሩትም የዚሁ ዘመቻ ኣካል ነው።
ሐ) የፌደራል ድህንነት መስራቤት= ለትግራዩ ኣንጃ ደግፈው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት የወረዳ ካቢኔ ኣመራሮች በሙስና ማስያዝና ማሳሰር ጀምረዋል። ለምሳሌ የምስራቃዊ ዞን የኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሃላፊዎች ከፈዴራል የመጡ የደህንነት ሰዎች እየታሰሩ ይገኛሉ። በትግራይ ሙሰኛ ታሰረ ከተባለ በፈጠረው ፖለቲካዊ ልዩነት እንጂ ከክልል እስከ ቀበሌ ያለው የሙሰኛ መዓት ከማሰር ህወሓት ማሰር ይቀላል።
መ) በትግራይ ክልል ያሉ ልማታዊ ባለሃብቶች የዘረፉትን የህዝብ ሃብት ከነሙሉ ሰነዱ በማሳየት ለኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ለመቃወም ከሞከሩ ዘብጥያ እንደሚገቡ እያሳይዋቸውና በድንጋጤ ሽባ የሆኑ ይገኛሉ።
ሰሞኑን ኣንድ ሚልዮን ብር ለልጁ ጥሎሽ የሰጠ የክልል ምክር ቤት ኣባል “ልማታዊ ባለሃብት” በመቐለ ከተማ በጣም ኣነጋጋሪ ሆኖ ከማለፉም በላይ የትግራይ ክልል ኣንጃ ደጋፊነት ተፈርጀዋል።
በመቐለ ከተማ በመጪው የህወሓት ጉባኤ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ከሚስታቸው ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ከስልጣናቸው እንደሚነሱ የተረጋገጠ መሆኑ እየተወራ ይገኛል።
የህወሓት ወደ ሁለት ኣንጃዎች የተከፈለችው ባለፈው ጉባኤ ሲሆን በወቅቱ የትግራይ ክልል ኣንጃ የነ ኣቶ በረከት ስምኦን ብኣዴን ድጋፍ ተብጅቶለት ባሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወቃል።
በኣሁነ ሰዓት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኣዲስ ኣበባ እየተካሄደ ይገኛል።
* ከታች ያለው ፎቶ የኣቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር ሲሆን ሰሞኑን በዓይጋ ፎሮም በትግርኛ ቃለ መጠይቅ ያካሄዱ ሲሆኑ በትግራይ ያለው ኣስከፊ የህወሓት ድክመት፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዲሞክራሲና ፀረ ሰላም ተግባና ባህሪ ፍንትው ኣድርገው በማሳየት በዓረና ኣባላት፣ የፌስቡክ ኣክቲቪስቶችና ባጠቃላይ በትግራይ ህዝብ ሲነገለት የበሩት ተግባራት በርሳቸው የደረሱ በደሎች ጭምር በማቅረብ በተለይ ህወሓት በጭፍን ሲደግፉ ለነበሩት ወገኖች ኣስደንጋጭ ምግ ግር ኣድርገዋል።
የነዚህ ሁለት የህወሓት ኣንጃዎች ኣሸናፊ ሁኖ የሚወጣው ቡዱን በትግራይና በትግራይ ህዝብ እንዲሁም በኢትዮዽያ ህዝብ የሚያመጣው ወይም የሚፈጥረው ተኣምር የለም። የኣቶ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ካሸነፈ የኣሁንዋ ትግራይና ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ይቀጥላል ማለት ነው።
የኣዲስ ኣበባ ኣንጃ ካሸነፈ ደሞ በኣቶ ፀጋይ በርሀ የነበረችው ትግራይ ተመልሳ ትመጣለች እንደማለት ነው። ማንኝዓውም ኣንጃ ካሸነፈ ወደ ስልጣን የሚመጡ ሰዎች ይቀያየሩ እንደሆነ እንጂ መሰረታዊ የሚባል ለውጥ ኣይኖርም።
ያው ወጮ ተገልበጥካዮ ወጮ ወይም ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣያጣፍጥም እንደሚባለው ነው። የትግራይ ወጣቶች የጀመራቹት ኣዲስ ዲሞክርሳሲያዊ ድርጀት የመመስረት ስራቹ ጥንክራቹ ግፉበት። ከዓረና ትግራይ ጎን ተሰልፈን ያለነውም ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ጓዶቻችን ሁነን ዲሞክራሲያዊት ትግራይና ኢትዮዽያ በትላችን እውን እንደርጋለን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Tuesday, August 4, 2015

ከፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ማግስት ….. ግርማ ሠይፉ ማሩ

Obama-in-ethiopiaኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አለበት? የለበትም? የሚለው አጀንዳ ማከራከሩ መቆም ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጥተዋል በቃ!! በእኔ እምነት ኦባማ ኢትዮጵያ የመጡት ኢትዮጵያ ባሳየችው ፈጣን ዕድገት ተመስጠው፣ ይህ ዕድገት ካፈራው ፍሬ የአሜሪካን ህዝብ እንዲቃመስ (ብዙዎቹ እንደሚሉት ቦይንግን እየገዛንም ቢሆን) ብለው አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ኦባማ ከስልጣን ከመልቀቃቸው በፊት የአባታቸውን ሀገር ኬኒያን መጎብኘታቸው በብዙ መመዛኛ የግድ አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ለዚህ አንድ መናጆ በቅርብ ያለች ኢትዮጵያ እንድትሆን የግድ የሚሉ ነጥቦች ተገኝተዋል፡፡ በዋነኝነት ደግሞ ሁሉቱ ሀገሮች በግንባር ቀደምትነት እየተፋለሙት የሚገኘው አልሸባብ የሚባለው የሽብር ቡድን ነው፡፡ በአሜሪካ መንግሰት ዘንድ ይህ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት የኦባማ ጉብኝት ፈቃድ እንዲያገኝ ይሁንታ ሊያስገኝ የሚችል ነጥብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ኦባማ በፀረ ሽብር ህጉ ህብረት አፍሪካዊያን በጋራ እንዲቆሙ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት በኩል ማስተላለፍ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚቻለው የሁሉም አፍሪካ ተወካዮች የሚገኙባት ሀገር ኢትዮጵያ እንደሆነች የሚስት የለም፣ ይህ ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ቁንጮ በሆነች ሀገር መሪ እንድትጎበኝ ዕድል ሰጥቷታል፡፡ እንዲህም ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም በጎ ነገር የለም የሚለው ነገር በፍፁም የለኝም፡፡
በእኔ እምነት ኦባማ አፍሪካን መጎብኘት ካለባቸው እና አምስት ሀገር መመርጥ ካለባቸው ኢትዮጵያ አንድ መሆን እንዳለባት አምናለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ካለኝ ግምት እንጂ ሀገሪቱን የሚመራው መንግሰት ኢህአዲግ ስለሆነ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያ የምትባል የሰው ዘር መገኛ የሆነች ድንቅ ሀገር ጎብኝተው ተመልሰዋል፡፡ ከዚህ ጉብኝት ምን ጠበቀን? ምን አገኘን? የሚለው ነገር በቅጡ መታወቅ አለበት፡፡ ይህ ጉዳይ ወደፊት በደንብ የሚፈተሸ ሲሆን አሁን ግን ካለብኝ ስጋት አንፃር አሳቤን ላጋራችሁ፡፡
እጅግ ብዙ የሚባሉ ምን አልባትም በፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አለን የሚሉ ሰዎች ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጥተው ይህን አንባገነን መንግሰት በአደባባይ እንዲያውግዙ እና ይህን የመሰለ ድርጊታቸውን የማያቆሙ ከሆነ ዲፕሎማሲያዊም ሆነ ከዚያ የዘለለ እርምጃ ሊወስዱ እንዲሚችሉ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡላቸው ነበር፡፡ ከዚያ በመነሳት ኦባማ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት “በዲሞክራሲያዊ አግባብ የተመረጠን መንግሰት በሀይል ማውረድ ተገቢ አይደለም” የሚለውን ቁንፅል ሃሳብ ይዘው ለምን አሉ በሚል ቡራ ከረዩ ሲባል ታዝቢያለሁ፡፡ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እንኳን ሰው ሀገር ለጉብኝት ሄደው አይደለም በሀገራቸው ቤተ መንግሰት (ኋይት ሀውስ) ተቀምጠው እንዲህ ዓይነት ከዲፕሎማሲ መስመር የወጣ የአንድን ሀገር መንግሰት ለማዘዝም ሆነ ለማስጠንቀቅ አይችሉም፡፡ በተለይ ኦባማ ከሚከተሉት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንፃር ይህ በፍፁም የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በሪፐብሊካን ዘመን ወዮልሽ ስትባል ከነበረችው ኢራን ጋር የተሻለ የሚሉትን መቀራረብ እና መነጋገር እንጂ ማስፈራራት ተገቢ አይደለም ብለው ይስራሉ፡፡ ኦባማ አሁንም ኢትየጵያ መጥተው ያስተላለፉት መልዕክት የኢትየጵያ መንግሰት አንባገነን ነው ብሎ በመራቅ ሳይሆን ቀርቦ በማነጋገር ማለዘብ ይቻላል ነው፡፡ ከቻይና ጋርም እንስራለን ሲሉን መልዕክቱ ግልፅ ነው፡፡ ኦባማ “በርማ” የሄዱት መንግሰቱ ዲሞክራሲያዊ ስለሆነ አይደለም፡፡ ኢትየጵያም የመጡት እንደዚሁ፡፡
የኦባማ ጉብኝት የአባታቸውን ትውልድ ሀገር ለመጎብኘት ካላቸው ቁርጥ አቋም ጋር መናጆ ተደርገን ነው የምንል ሰዎችም ብንሆን የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ምንም የሚያመጣው ፋይዳ የለም የሚል እምነት የለንም፡፡ ይህን ፋይዳ ግን ገዢው ፓርቲ እና መንግሰት እንዴት ይጠቀሙበታል የሚለው ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ በዋነኝነት ይህን ጉብኝት መጠቀም የጀመረው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እና ይህን ጉብኝት የተቃወሙትን በተለይ ግልፅ ተቃዎሞ ሲያሰሙ የነበሩትን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለማውገዝ እና ለማሸማቀቅ ነው፡፡ ይህ ትርፍ ከአስገኘም የአጭር ጊዜ እንጂ ዘላቂ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል ሳይሆን መቃቃርን የሚያፋፋ አካሄድ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኦባማ ጉብኝት ትርፍ በአፍንጫችን ቢወጣ ይሻለን ነበር፡፡ ከዚህ መንግሰት ባህሪ አንፃር ከኦባማ ጋር በሚስጥር በተደረገ ውይይት መነሻ የሚደረጉ ፈጣን የፖሊሲም ሆነ የአስራር ለውጥ በግሌ አልጠብቅም፡፡ ምክንያቱም “ኦባማ እንዲህ አድርጉ ብሎ አደረጉ” መባል አይፈልጉም፡፡ በሌላ ፅንፍ ያሉትም ቢሆኑ “ኦባማ አዟቸው አደረጉ” ማለታቸው አይቀርም፡፡ ይህ በኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሲታይ ፊት ለፊት ያለው ሲሆን ይህ ደግሞ ለለውጥ እጅግ ደንቃራ የሆነ አስተሳሰብ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህን ሊሰብር የሚችል መሪ ያለን አልመሰለኝም፡፡ አግኝተን ግምቴ ልክ ባይሆን ደስ ይለኛል፡፡
ሌላው ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝት ከፍተኛ ጥቅም ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው በገፅታ ግንባታ እና እርሱን ተከትሎ የሚመጣው የግል ባለ ንዋዮች የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ከፕሬዝዳንቱ ጋር እጅግ ብዙ ጋዜጠኞች ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ገፅታ በሚችሉት መስመር ሁሉ ለማግኘት እንደሞክሩ ይታመናል፡፡ እነርሱን መሰረት አድረገው መረጃ የሚተነትኑ እና የሚያወጡ አካላት የሚሰጡት ግመገማ ውጤት ለኢንቨስተሮች ውሳኔ መሰረት ሆኖ ያገለግላል፡፡ የአሜሪካና የቻይና መሪዎች በሀገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ ጉልዕ ልዩነት አለ፡፡ የቻይና ፕሬዝዳንት መጥተው ጉብኝት አድርገው ቢሄዱ አንድ ቃል ሊገቡ የሚችሉት ነገር ይኖራል፡፡ መንግሰታቸው ከሚመሯቸው ተቋማት የተወሰኑትን በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት አድርጉ ብለው ትዕዛዝ ሊስጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ፕሬዝዳን ባራክ ኦባማ ይህን ለማድረግ እድልም መብትም የላቸውም፡፡ የአሜሪካ ባለሀብቶች ከመንግሰታቸው ጥበቃን እንጂ የት ኢንቨሰት እንደሚያደርጉ መመሪያ አይሰጣቸውም፤ አይቀበሉም፡፡ የሚገርመው በራሳቸው ውሳኔ ባደረጉት የኢንቨስትምንት ውሳኔ ግን መንግስታቸውን በቂ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ያስገድዱታል፡፡ ይህ ነው የአሜሪካ ስርዓት፡፡
የኢትዮጵያ መንግሰት ከኦባማ ጉብኝት ውጤት ይጠብቅ ከሆነ ያለ ምንም ይሉኝታ በሀገራችን የግል ኢንቨስትመን (በተለይ የውጭ) እንዳይመጣ ማነቆ የሆነውን የውስጥ ሰላምን (ፀጥታ አላልኩም) ማምጣት አለበት፡፡ ይህ ማለት በጠምንጃ ታፍኖ ዝም ያለ ህዝብን መፍጠር ሳይሆን በዲሞክራሲያዊ ሰርዓት ውስጥ የሚገኝ ስላምን መፍጠር ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም ዋነኛ ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉትን ነፃ ሚዲያ፣ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታን፣ በህገ መንግሰት ላይ የተደነገጉትን የስብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፣ ልዩነቶች በህጋዊ አግባብ መፍታት የሚቻልበት የፍትሕ ሰርዓት መዘርጋት፣ ወዘተ እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ሲሟሉ የአውሮፓና አሜሪካ ባለሀብቶች ይመጣሉ፣ ኦባማም ኢትዮጵያን ባይጎበኙም፡፡
ኦባማ በአፍሪካ የስልጣን ገደብ ማጣት፣ ሙስና፣ የነፃው ፕሬስ እመቃ ወዘተ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ካንሰር መሁኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡ የሚገርመው መሪዎቻችን ያጨበጭቡ ነበር፡፡ ታመሃል ሲባል የሚያጨበጭብ ታማሚ አንባቢ ልብ ሊለው ይገባል፡፡ በአኔ እምነት በካንሰር የተያዘ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ በሚገኝ ኢኮኖሚ ውስጥ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚመጣ ይኖራል ማለት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከኦባማ ጋር የመጡት የልዑካን ቡድኖች ውስጥ የሚገኙት የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች በኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ፓርቲ አንባገነን ስርዓት እንዳለ አይሰሙም፣ በሲቪክ ማህበረስብ ውስጥ እየተደረገ ስለ አለው እመቃ አይረዱም፣ ከሲቪል ማህበራት ጋር የተደረገው ውይይት በሚዲያ ሳይገለፅ በሚስጥር ውይይት ይደረግበት ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ አይገባቸውም ማለት እነዚህ ባለ ሀብቶች በሚወስዱት ውሳኔ ሳይሆን በድንገት ባለሀብት የሆኑ ያስመስላል፡፡ ኢቲቪ ማታለል የሚችለው በኢቲቪ መረጃ መሰረት አድርገው ውሳኔ ለሚያሳልፉ ብቻ ነው፡፡
በኦባማ ጉብኝት ምክንያት አንድ የተገኘ ውጤት አለ፡፡ ይህ ውጤት ለአሜሪካም ለኢትዮጵያም እኩል ነው ብለን አናምንም፡፡ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግስታት ባስማማቸው ጉዳይ ላይ ቃል ኪዳናቸውን አድሰዋል፡፡ ከዚህ በፊት በሚስጥር ተይዞ የነበረው የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የፀረ ሽብር (በተለይ አልሻባባም በሚመለከት) ኃይል ግንባር መሪ መሆን አሁን በይፋ ታውጇል፡፡ ለዚህም የሚያስፈልገውን ሁለቱም መንግሰታት ለማዋጣት አቅሙ አላቸው፡፡ እኛ ደምና ነብሳችንን እነርሱ ደግሞ ዶላር ሊሰጡን ተሰማምተናል፡፡ በዚህ አጀንዳ ዙሪያ በሁለቱ መንግሰታት ዘንድ ልዮነት የለም፡፡ ይልቁንም ሁለቱ ሀገራት በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ባላቸው የጫጉላ ጊዜ ሌሎች አጀንዳዎች እንዲገፉ እና በተለይ የኢትዮጵያን የግፍ ቀን እንዲረዝም በር ከፍተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰት አልሻባብና መሰሎችን ብቻ ሳይሆን ለዲሞክራሲ የምጮሁ ኢትዮጵያዊያንንም ከእነዚህ ጋር ቀላቅሎ ለመውቀጥ አስፍስፎ ይገኛል፡፡ እሰከ ዛሬ የበላቸውን እነ አንዱዓም አራጌን፣ ናትናኤል መኮንን፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽን፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ወዘተ ጨምሮ ማለት ነው፡፡
የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንበታን በሚመለከት አሜሪካኖች ምክር የሚሰጡ ሲሆን የወዳጅ ምክርን መስማት ያለመስማት ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሰት እጅ የሚገኝ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መንግሰት አተያየ በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም አገላለፅ “እንቁላል በአንድ ቅርጫት” አይቀመጥም፡፡ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ወዳጅ አንድ አይበቃም፡፡ ከቻይናም ከአሜሪካም ያስፈልጋል፡፡ አንዱ ቢያኮርፍ በአንዱ የሚል ዘይቤ ተጀምሮዋል፡፡ ኦባማ ማኩረፍና መራቅ አይጠቅምም- መነጋገር ነው የሚያዋጣው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰት ምንም ግልፅ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢፈፅም፣ ከዓለም ሁለተኛ ሚዲያ አፋኝ መንግሰት ቢሆኑም ኢትዮጵያን ከሚመስል ትልቅ ሀገር ጋር ጠብ አያስፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰትም ቢሆን አሜሪካ ምንም እንኳን ኒዎሊብራል የሆነች ሀገር ብትሆን እና በሀገሯ ኢኮኖሚያዊ ፍትህ የሚያሰፍን መንግሰት ሳይሆን ገበያ የሚመራት ቢሆንም፣ አይንሽን ላፈር ብሎ መሳደብ ጥቅም የለውም፡፡ ሰለዚህ ሁለቱ መንግሰታት የጫጉላ ጊዚያቸውን በሚያስማማቸው ጉዳይ ላይ ያደርጋሉ፡፡ የእኛ ደምና ነብስ እንዲሁም ዲሞክራሲያዊና ስብዓዊ መብታችን አሳልፎ መስጠት፣ የአሜሪካኖች የታክስ ከፋይ ገንዘብ ለጊዜውም ቢሆን ጋብቻ ፈፅመዋል፡፡
ቸር ይግጠመን


በአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ትግል ላይ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ያሉ ፈተናዎችና ማርከሻ መድኃኒታቸው!

ginbot 7ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እግዚአብሔር ይመስገንና አሁን የነገዋን ነጻይቱን ኢትዮጵያ ለማየት መንገዱ ላይ ቆመን መራመድ የቻልንበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄ ትልቅ ትልቅ እመርታ ነው፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ ራሱ ወያኔ ተሸንፎ እንደወደቀ መቁጠር ይቻላል፡፡ የቀረው የባለሥልጣኑ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ነገ የሚሆነው ነገ እንጅ ዛሬ ስለማይሆን ብቻ ነው፡፡ ነገ ግን ዛሬ መሆኑ አይቀርምና ነገ የምንጨብጠውን ዛሬ እንደጨበጥነው መቁጠር ይቻላል፡፡
ይህ ታላቅ እመርታ እንዳይመዘገብ ወያኔ የሀገር ክህደት በመፈጸም ለጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊ የሀገሪቱን መሬት እየቆራረሰ ከመስጠት ጀምሮ በተለያየ ጥቅም በመያዝ መሸሻ መሸፈቻ መደራጃ መንቀሳቀሻ መንደርደሪያ እሱ ሱዳንን ይጠቀምባት እንደነበረውና ከሱዳን ያገኝ የነበረውን ድጋፍና ምቹ ሁኔታዎች የሚሰጠን ጎረቤት ሀገር እንዳይኖርና እንዳናገኝ ለማድረግ ያላደረገው ነገር ያላስቀመጠው መሰናክል ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም፡፡ ይሄንን ዕድል ልናገኝ የምንችልበት አንድ ቦታ ከተገኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶተኛ ከመሆኑና ይሄንን አጋጣሚ የሚጠባበቅ ከመሆኑ የተነሣ አርፎ ተቀምጦ የነበረውም አማራጭ ስላጣ ብቻ እንደሆነ ይሄንን ዕድሉን ባገኘ ጊዜ ግን ወያኔ ዕድሜ እንደማይኖረው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያልቅለት ጠንቅቆ ያውቀዋልና፡፡ መሸሻ መሸፈቻ ለማሳጣት ይሄንን ያህል ርቀት የተጓዘው ወያኔ ይህ አሁን ከባሕረ ምድር (ኤርትራ) ላይ ያገኘነውንም ለማሳጣት ለማበላሸት ይሄም አልሆን ሲለው ሐሰተኛ የፈጠራ ወሬና ሴራ በመጠንሰስ እንድንሸሽና እንዳንጠቀምበት ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ሲጥር ነበር እየጣረም ይገኛል፡፡ እውነቱን መለየት ማወቅ መረዳት እስኪያቅተን ድረስ ባሕረ ምድር የመሸጉትን የነጻነት ታጋዮችን ትግል ሊያደናቅፍ ሊያሰናክል ሊያጨናግፍ የሚችሉ የሆኑና ያልሆኑ ነገሮችን መሠረት ያደረጉ ስሞታዎችን ስም ማጥፋቶችን ድምዳሜዎችን የያዙ መጣጥፎች አሁን ማንነታቸው ይበልጥ ግልጽ እየሆኑ እየታወቁ በመጡ ግለሰቦች ቀደም ሲል ግን በጣም ተአማኒነት በነበራቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ድረ ገጾች ላይ እየተለቀቁ እየቀረቡ ትግሉን እንድንጠራጠር እንዳናምን እንድንሸሽ ከዚያም አልፎ በጠላትነት እንድንፈርጅ ለማድረግ ከባድ ከባድ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
ከዚህ በኋላም ወያኔ እስካለ ድረስና የዕጣ ፈንታው የመጨረሻ መጨረሻ ሰዓት የደረሰ መስሎ እስከታየው ድረስ አያደርገውም የሚባል ነገር ሳይኖረው ሊያደርገው የማይችለው ምንም ዓይነት ነገር ሳይኖር እስከ የመጨረሻ ህቅታው ድረስ የጣረሞቱን በመንፈራገጥ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም የተቻለውን ሁሉንም ዓይነት ጥረቶች በማድረግ ይቀጥላል እንጅ ይቆማል ብላቹህ አታስቡ፡፡ አሁን አሁን ከእነዚያ ስም ማጥፋቶች የተጋነኑ ስሞታዎችና የፈጠራ ውንጀላዎች ትክክለኛ የተፈጸሙ ከሆኑትም ጀርባ የወያኔ እጅ እንዳለ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔ በእርግጥ ጥርጣሬው የነበረኝ ቢሆንም አብዛኞቻችን ይሄንን አለመገመታችን አለመጠርጠራችን ምን ያህል የዋሆች ብንሆን ነው እያሰኘኝም ነው፡፡
እነኝህን ጽሑፎች ይጽፉና በድረ ገጻቸው ይለጥፉ የነበሩ ግለሰቦችና ድረ ገጾች አንዳንዶቹ አስቀድሞ በነበረው ማንነታቸው በወያኔነት የምንጠረጥራቸው አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ ግን ወያኔ በስውር ለዚሁ ዓላማው አስቀድመው ተአማኒነትን አግኝተው እንዲቆዩ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በወያኔነት የማንጠረጥራቸው ወይም ወያኔ ያልነበሩትም ቢሆኑ ትናንት አልነበሩም ማለት ዛሬ አይሆኑም ማለት አይደለም፡፡ ወያኔ የመጨረሻው መጨረሻ የደረሰ መስሎ ከታየው እራሱን ለማዳን የሚቆጥበውና የሚሰስተው ምንም ነገር የለም፡፡ እንዳልኳቹህ የሀገርን ካዝና አራቁቶም ቢሆን ገንዘብ ይረጫል፣ ፍላጎታቸው ገንዘብ ሳይሆን ጉዳዮች እንዲፈጸምላቸው ለፈለጉት ጉዳዮቻቸውን ይፈጽምላቸዋል፣ ፍላጎታቸው እነዚህ ሁቱም ያልሆነና ሥልጣን ለሚፈልጉትም ከሚንስትርነት እስከ ዲፕሎማትነት (አቅናኤ ግንኙነት) ድረስ ሥልጣን እየሰጠ ይደልላል፡፡ ሌላው ቀርቶ አያገኝም እንጅ እንዲህ አድርገሀል እንዲህ ብሎ ለፍርድ ላቅርብህ ሳይለው ከሀገር ክህደት እስከ የዘር ማጥፋት ለፈጸመው ወንጀል ላይጠይቀው አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጠው አካል ቢያገኝ የመንግሥት ሥልጣንን ሁሉ አሳልፎ በመስጠት እራሱን ለማዳን ዝግጁ ነው፡፡
አሁን በዚህ ዘመን በእነዚህ ወያኔ ያንዣበበበትን አደጋ ለማስቀረት ሳይሰስት በሚያቀርባቸው መደለያወች የማይለወጥ የማይደለል ሰው ማግኘት በጣም ከባድ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሣ ብዙዎች ያውም በቀላል በቀላል ነገር እየተደለሉ ሕዝብን እንደካዱ ስናይ ቆይተናል፡፡ አብሶ ደግሞ ሀገርና ሕዝብ ነጻ ሆነው ማየት ቁርጠኛ ዓላማ ይዞ ሳይሆን ከግል ጥቅሙ ከዝናና እውቅና ፍለጋ አኳያ እንዲሁም ወያኔ ተወግዶ እሱም ሥልጣን ይዞ በተራው ባለ ሥልጣን ለመባል፣ ለመኮፈስ፣ ሕዝብን ከጫማው ስር ለመርገጥ፣ በግል ጉዳዩ ለገጠመው ችግር የተጣላውን ለመበቀል፣ ለማዘዝ ለመናዘዝ ወይም ደግሞ ለመብላት ምኞትና ፍላጎት ይዞ በተለያዩ የሕዝባዊ ትግል ዘርፎች ተሰማርቶ ወያኔን እየተገዳደረ እየተሯሯጠ ያለ ሰው ከሆነ እንዲህ ዓይነቱን ሰው የያዘውን ሕዝባዊ ትግል በማስካድ ወያኔ የሚፈልገውን ነገር አቅርቦለት አድርጎለት ደልሎ መጠቀሚያው አገልጋዩ እንዲሆን ለማድረግ አይቸግረውም፡፡ አሁን እያስቸገሩ ያሉ ግለሰቦች የተደለሉበት ገንዘብ ወይም ሌላ የመደለያ ነገር መጠንና ዓይነት ይለያይ እንደሆነ ነው እንጅ ከላይ የጠቀስኩትን ዓይነት ፍላጎቶች ይዘው በተለያየ መስክ ሕዝባዊ ትግል ያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ላይ እኛ ሳናውቃቸው ቀርተን እራሳቸውን ሰውረው ወያኔ ደልሎ ለራሱ ጥቅም እንዲያድሩ ያደረጋቸው ግለሰቦች አሳቢ መስለው የተለያየ ነገር በማውራት የትጥቅ ትግሉ እንዳይታመን እንዳይጠነክር ከግብ እንዳይደርስ ለማድረግ ይጠቀሙባቸው በነበሩ ሐሳቦች ላይ አተኩረን ዕናያለን፡፡ ወደ መሀሉም ወያኔ ገዝቷቸው ካልሆነ በስተቀር ሌላ አሳማኝ ምክንያት ስላላቸው እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ትግል የሸሹ እንዳልሆኑና ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት አቅርበው ሊሸሹ ሊቃወሙ የማይችሉበትን አመክንዮም ዕናያለን፡፡
የትጥቅ ትግሉን የሚቃወሙ ወገኖች የትጥቅ ትግሉን ተአማኒነት ለማሳጣት የሚያነሡዋቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው? የሚለውን ቀድመን ዕንይ በአምስት ዋና ዋና ሐሳቦች ይጠቀለላሉ፡-
  1. ሸአቢያ ራሱ ስላልቻለ አቅም ስለሌለው በእኛ ተጠቅሞ ወያኔን ለመበቀል ለማስወገድ ነው እንጅ በፍጹም በፍጹም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ በማሰብ ይሄንን ድጋፍ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሸአቢያ በዚህ ዓላማው ምክንያት በሚያደርግልን ድጋፍ ውጤት ቢመጣ እሱ እንጅ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አትሆንም፡፡
  • የወያኔና የሸአቢያ ፀብ የውሸት እንጅ እውነተኛ አይደለም እዛ ብንሔድ መልሶ ነው አሳልፎ ለወያኔ የሚሰጠን ወይም የሚፈጀን፣ ፀባቸው የእውነት ቢሆንም ወያኔና ሸአቢያ ቀደም ሲል ከነበራቸው ጥምረት ቁርኝትና ዝምድና አንጻር ለሸአቢያ ከወያኔ ይልቅ እኛ ቀርበነው ይሄንን ያህል ውለታ ሊውልልን አይችልም፣ ሊታመንልን አይችልም፣ ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው ብሎ ከመጠራጠር፡፡
  • የታጠቀ ኃይል የምንፈልገውን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፣ በአፈሙዝ የሚገኝ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) የለም፣ የታጠቀ ኃይል የራሱን እንጅ የሕዝብን ፍላጎት አያሟላም፡፡ ከሚል ዓለም አቀፋዊውን ነባራዊ ሁኔታ ካልተገነዘበ አስተሳሰብ፡፡
  • በዘመነ ደርግ ወያኔና ሸአቢያ ደርግን ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የስንቅና ትጥቅ (logistics) ሌላም ድጋፍ ያደርጉላቸው እንደነበሩ ሀገራትና አንዳንድ አካላት በዚህ ዘመን ለእኛ ሊያደርግልን የሚችል ባለመኖሩ በቂ ስንቅና ትጥቅ ሊገኝ ስለማይችል ከንቱ ድካምና ከንቱ መሥዋዕትነት ነው ከሚል፡፡
  • ሸአቢያ እኛን ይዞ ወያኔን ለማስፈራራትና ከወያኔ የሚፈልገውን ለማግኘት እንጅ የምናደርገው ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ለስኬት እንዲበቃም በፍጹም አይፈልግም፡፡ የሚሉ ምክንያቶችን ያቀርባሉ፡፡
እነኝህ ሥጋቶች ጥርጣሬዎችና ስሞታዎች ተጨባጭና ትክክለኛ ስለመሆናቸው መፈተሽ ይኖርብናልና እንደ ቅደም ተከተላቸው እንፈትሻቸው፡-
  1. “ሸአቢያ ራሱ ስላልቻለ አቅም ስለሌለው በእኛ ተጠቅሞ ወያኔን ለመበቀል ለማስወገድ ነው እንጅ በፍጹም በፍጹም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ በማሰብ ይሄንን ድጋፍ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሸአቢያ በዚህ ዓላማው ምክንያት በሚያደርግልን ድጋፍ ውጤት ቢመጣ እሱ እንጅ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አትሆንም” የሚባለው ነገር ሸአቢያ እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ሊኖረው ቢችልም እንኳን የእኛ ጠላት የሆነው ለሸአቢያም ጠላት መሆኑ ጥሩ ዕድል መፍጠሩን በመረዳት የጋራ ጠላትን አንድ ግንባር ፈጥሮ ወይም ተረዳድቶ ማጥቃቱ ማጥፋቱ ስልታዊ አኪያሔድ እንጅ ጉዳቱ ምኑ ላይ ነው? ይሄንን ሥጋት የሚያነሡ ወገኖች ይሄንን ያላቸውን ሥጋት በደፈናው ከመናገር በስተቀር ወያኔ በዚህ ጥምረትና መረዳዳት ቢጠፋ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የማትሆንበትን ምክንያት በግልጽ እንዲህ እንዲህ ነው በማለት አያስረዱም፡፡ በደፈናው ከመጠራጠር በስተቀር የሚሉት ነገር የላቸውም፡፡ ስገምት ግን የእነሡ ሥጋት “ወያኔ ሲወድቅ በወያኔ ቦታ ሸአቢያ ይቀመጥና ውጤቱ ጉልቻ መለዋወጥ ነው የሚሆነው” የሚሉ ይመስላል፡፡ ይሄም ቢሆን ግን ሥጋቱ ተጨባጭ አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች የተባለችው ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንደ አንድ ሀገር አውቄሻለሁ ብሏታል ከተባለ በኋላ ሸአቢያ አዲስ አበባ ገብቶ ሥልጣን ሊይዝ የሚችልበት ምንም ዓይነት ሁኔታ አጋጣሚ አሠራር የሌለና ሊታሰብም የሚችል ባለመሆኑ ተደርጎ ቢገኝም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕግ መሠረት “ወረራ” ተብሎ የሚወገዝና ወረራው በአባል ሀገራት የትብብር ጥቃት እንዲቀለበስ የሚደረግ በመሆኑ ሥጋቱ ተጨባጭ ያልሆነና ሊገመትም የሚገባ አይደለም፡፡
  2. “የወያኔና የሸአቢያ ፀብ የውሸት እንጅ እውነተኛ አይደለም እዛ ብንሔድ መልሶ ነው አሳልፎ ለወያኔ የሚሰጠን ወይም የሚፈጀን፣ ፀባቸው የእውነት ቢሆንም ወያኔና ሸአቢያ ቀደም ሲል ከነበራቸው ጥምረት ቁርኝትና ዝምድና አንጻር ለሸአቢያ ከወያኔ ይልቅ እኛ ቀርበነው ይሄንን ያህል ውለታ ሊውልልን አይችልም፣ ሊታመንልን አይችልም፣ ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው ብሎ ከመጠራጠር” ይሄ ደግሞ በጣም አስቂኝ ነው፡፡ ሰው አይጠርጥር አይጠንቀቅ አይባልም በተለይ በእኛ ሁኔታ መጠራጠርና መጠንቀቅ ተገቢና አስፈላጊም ነው፡፡ ነገር ግን የጠረጠርነውን ነገር ሊያስወግዱ ሊቀርፉ የሚችሉ ያሉና የሚታዩ ተጨባጭ ኩነቶች ባሉበት ሁኔታ አንድ ሰው በዚህ ደረጃ ተጠራጥሮ የማይመስል ነገርን ሲያስብ ብታገኙት ይሄ ሰው በጤነኛና ትክክለኛ የአእምሮ ጤና ውስጥ እንዳልሆነ እርግጠኛ ልትሆኑ ትችላላቹህ፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት መስመር የሳተ አስተሳሰብ የሚዳረጉ ሰዎች እንዲህ ሊሆኑ የሚችሉበት ምክንያት ሲመረመር እንዲህ ብለው በሚጠረጥሯቸው በሚያስቧቸው አካላት ከባድ የሥነልቡና ጫና መታወክና መረበሽ የደረሰባቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡ ከዚህም የተነሣ እነዚያን የሚጠረጥሯቸውን አካላት በተመለከተ ሊያደርጉትና ላያደርጉት ሊችሉትና ላይችሉት ሊሠሩትና ላይሠሩት ይችላሉ ብለው የሚያስቡት የሚገምቱት ሲመረመር ከሞላ ጎደል ትክክለኛ ሆኖ አይገኝም፡፡ ሥጋቶቻቸውና ጥርጣሬዎቻቸው ከታወከ ሥነልቡናቸው የሚመነጩና ከገሀዱ ዓለም ተጨባጭ እውነታዎች የራቁ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ያሉ ነገሮችንም በተጨባጭ ካሉ ከተፈጸሙ መሬት ላይ ከሚታዩ ነገሮች አንጻር መመዘን መለካት የሚፈልጉ አይደሉም፡፡
ይሁንና ምናልባት ያሉበትን ተጨባጭ ያልሆነ ምናባዊ አስተሳሰብ ማሰብ ማገናዘብ መረዳት ያስችላቸው እንደሆነ ከሚል እንዲህ ለሚሉ ሰዎች ላነሣቸው የምፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉኝ፡- ሀ. የሸአቢያና የወያኔ ጸብ የውሸት ከሆነ የዚህ የውሸት ጸባቸው ምክንያት ዓላማና ግብ ምንድን ነው? ለ. ጸባቸው የውሸት ከሆነ ወያኔና ሸአቢያ ለ17 እና ለ30 ዓመታት ደርግን ሲታገሉ ከእያንዳንዳቸው ወገን ካለቀባቸው ሠራዊት በላይ በዚያች በአጭር ጊዜ ጦርነት ባደረጉት ጦርነት ብቻ ከእያንዳንዳቸው ወገን ሰባ ሰባ ሽህ የሚገመት ሠራዊት ላለቀበት አስከፊ ጦርነትስ እንዴት ሊዳረጉ ቻሉ? ሐ. ከዚያ አሰቃቂ ጦርነት በኋላስ ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ከዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ተነጥላ በማዕቀብ ስር ሆና ሕዝቧም ለአስቸጋሪ የድህነት ኑሮ ተዳርጎ እስከ አሁንም ድረስ በከባድ ችግር ለማለፍ እንዴት ልትገደድ ቻለች? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሳቸው ለመመለስ ቢሞክሩ ጭንቅላታቸውን ወደ ትክክለኛውና ጤነኛው አስተሳሰብ ለመመለስ ይረዳቸው ይሆናል ብየ አስባለሁ፡፡ አንዱ እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት “ጋዜጠኛ” እማ ጭራሽ ምን አለ? “ጸባቸው የውሸት ነው” ካለ በኋላ “የውሸት መሆኑንም የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያ ለኤርትራ በየዓመቱ 250 ሚሊዮን (አእላፋት) ዶላር ትረዳለች” በማለት ያለበትን የሥነልቡናና የሥነ አእምሮ የጤና መታወክ ደረጃ ቁልጭ አድርጎ ሊያሳየን ቻለ፡፡ ወይም ደግሞ የትጥቅ ጥግሉን ለማክሸፍ ለስውር ተልእኮ ወያኔ ከቀጠራቸው ቅጥረኞች አንዱ መሆኑን እንዲህ በል ተብሎ ሊሆንም ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ያለው ነገር የፈጠራ መሆኑን የሚያረጋግጠው አስቀድመን ከጠቀስናቸው የሸአቢያና የወያኔ ፀብ የውሸት አለመሆኑን ከሚያረጋግጡት ነጥቦች አኳያ የማይመስል ነገር መሆኑና ለወሬው መረጃውን ወይም ምንጩን መጥቀስ ያልቻለ መሆኑ ነው፡፡
ሌላው “ሸአቢያ ታማኝ አይደለም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሴረኛ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው” ለሚለውን የዋሀን ወገኖቻችንም ይሄንን አጥብቀው ያነሣሉ፡፡ ለነገሩ እነሱን ጨምሮ የወያኔ ካድሬዎችም ጭምር ሸአቢያ ከወያኔ የባሰ ጠላት ለመሆኑ የሚጠቃቅሷቸው ነገሮች አሉ፡፡ በሸአቢያ በኩል ደግሞ እነኝህ የሚጠቀሱ ነገሮች ሐሜቶችና የወያኔ የፈጠራ ወሬዎች መሆናቸውንና እሱ ግን ከድሮ ጀምሮ ለኢትዮጵያ በማሰብ ቀና ቀና ነገሮችን ሲያደርግ እንደቆየ ቢናገርም እንዲያው አንዳችም የፈጸመብን ክፉ ተግባር የለም ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ምንስ ቢሆን ሲዋጋ የኖረው ከእኛ ጋር መሆኑ ቀረ እንዴ! ጠላቱ አድርጎ የሚያስበንን ለመጉዳት ለማጥቃት ለማዳከም የማይመኘን የማይጥርብን ምን ያህል ታጋሽ አርቆ አሳቢ በሳል ይቅር ባይ ቢሆን ነው? እንኳንና የሚጠቀሱ ነገሮች እያሉ የቱንም ያህል ደግ አሳቢ ቅኖች የነበሩ ቢሆኑም እንኳ የዚህን ያህል ሊያመጻድቅ የሚችል ሥራ ሊኖራቸው እንደማይችል መገመት የሚቻል ይመስለኛል፡፡
ነገር ግን ይህ የሸአቢያ መልካም ሥራ እውነት መሆኑን ማጣቀሻዎችን እያነሡ የመሰከሩ የአንዳንድ ወገኖች ምስክርነትንም ሰምተናል፡፡ እንደኔ እንደኔ ሠራው የተባለው ክፋት እውነት ቢሆንም እንኳን ሊያስደንቀን የሚገባ አይደለም፡፡ በጠላትነት ተፈራርጀን ስንተላለቅ የኖርን ሰዎች ሆነን እያለ አንዳችም ክፉ ነገር እንዲያደርግብን መጠበቅ የኛን የዋህነት ሊያስይ ቢችል እንጅ ሊሆን የባይገባው ነገር መደረጉን የሚያሳይ አይመስለኝም፡፡ ምን ነካቹህ? በቀንደኛ ጠላትነት ተፈራርጀን ለ30 ዓመታት እኮ ነው ጦርነት ስናደርግ የኖርነው! እኛ እነሱን ልናጠፋ እነሱም እኛን ሊያጠፉ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ያ ትግላቸው ለስኬት አብቅቷቸው የትግላቸውን ፍሬ እየለቀሙ ያሉበት ደረጃ ላይ በመሆናቸውና ትግላቸው “ያተረፉበት ወይስ የከሰሩበት? መሆን መደረግ የነበረበት ወይስ ያልነበረበት?” የሚል ጥያቄን ለራሳቸው እንዲያነሡ የተገደዱበት ወቅት ላይ ያሉ በመሆኑና ለትግል ያስወጣቸው ችግሮች የነበሩ ከሆነም እንኳን እነዚያን ችግሮች በሌላ መንገድ መፍታት ይቻል የነበረበትን አማራጭ መፈለግ የተሻለ እንደነበር የተረዱበት ወቅት ላይ ያሉ በመሆናቸው እድሜ የማያስተምረው የማያበስለውም የለምና ከዕድሜና ከተሞክሮም በመማራቸው ከዚህ አንጻር በዚያ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የሠሩት የፈጸሙት ሸር ሴራ ወንጀል ተንኮል ክፋት ቢኖርም እንኳን የሚጸጸቱበት እንጅ የሚኮሩበት ባለመሆኑ እንደቀድሟቸው ሁሉ አሁንም እንደዚያው ያደርጋሉ ያስባሉ በማለት ፍጹም አትጠራጠሩ ባልልም ድምዳሜ ላይ መድረሱ ግን የሚገባ ነው ብየ አላስብም፡፡
የወያኔ ካድሬዎች ተቀጣሪዎችና የዋሀን ወገኖች የፈለጉትን ሲያወሩ ለሸአቢያ የነበረን ሥዕል ከድሮው መጥፎ መሆኑ ስለ ሸአቢያ መጥፎነት ምንም ነገር ቢባል በቀላሉ እንድናምን እያደረገን ወደ እውነቱ እንዳንደርስ የተጫነን መስሎ ይሰማኛል፡፡ እኔ እንዲያውም አሁን አሁን እየተረዳሁት የመጣሁት ነገር ቢኖር በሸረኝነት በክፋተኝነት በጠንቀኝነት በሴረኝነት በጠላትነት ወያኔ ሸአቢያን እጥፍ አስከንድቶ የሚበልጠው መሆኑን እንጅ የሚያንሰው አለመሆኑን ነው፡፡ በግልጽ አማርኛ ከመጀመሪያውም ጀምሮ ከሸአቢያ ይልቅ ወያኔ እጅግ በጣም የከፋ ሸረኛ ሴረኛ ክፉ ጠላት ነው፡፡
ይሄንን ልታረጋግጡ የምትችሉበትን አንድ ሁለት ነገሮችን ላንሣላቹህ፡፡ ከ1990ዓ.ም. የወያኔ ሸአቢያ ጦርነት በኋላ እነ አቶ ኢሳይያስ ከዓለሙ ማኅበረሰብ የተነጠሉ መሆናቸውን ታውቃላቹህ፡፡ ለምዕራባዊያን ከኢትዮጵያ ይልቅ ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ስልታዊ (strategic) ጠቀሜታ ያላት ነች፡፡ የወያኔ ሸረኝነት ሴረኝነትና ዋሽቶ የማሳመን ችሎታ ከሸአቢያ እጅግ የላቀ መሆኑ ባሕረ ምድር እንዲህ ዓይነት ስልታዊ ጠቀሜታ ያላት መሆኗ በቀላሉ ምዕራባዊያንን ከጎኗ ማሰለፍ የሚያስችላት ሆኖ ሳለ በጠቀስነው ችሎታ ወያኔን ስላልቻሉትና በዲፕሎማሲው (በአቅንኦተ ግንኙነቱ) ላይ የበላይነቱን በመያዙ ከጨዋታ ውጪ እንዳደረጋቸው ዓይተናል፡፡ ይሄው እስከዛሬም በአሳዛኝ ተሸናፊነት ተገልለው እንዲቀሩ አድርጓቸው ቀርቷል፡፡ ከሸአቢያ ያየነው ብቃት ቢኖር የዘመኑን የፖለቲካ ጨዋታ ባለመረዳት ከሁኔታዎች ጋር እንደወያኔ እየተጣጠፈ በብልጠት ጥቅሙን ማስከበር ሳይችል በግትርነት በድርቅና መጽናቱን ብቻ ነው፡፡
ይሄ ሽንፈት በድንበር ዳኝነቱ (ኮሚሽኑ) ውሳኔ ጊዜም ተደግሟል የዳኝነቱ ውሳኔ ትክክል ባይሆንም የድንበር ኮሚሽኑ (ዳኝነቱ) ይግባኝ በሌለው ውሳኔ ባድመን ለባሕረ ምድር የወሰነ ሆኖ እያለ ከሸአቢያ ችሎታ ማነስና ደካማነት ከወያኔ መሠሪነት ሸረኝነት የተነሣ ውሳኔው ተፈጻሚ መሆን እንዳይችል አድርጎታል፡፡ እንግዲህ ሸአቢያ ሊጠቀምባቸው መብቴ ነው የሚለውን ሊያስጠብቅበት የሚያስችለው ዕድሎችና አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩትም ከደካማነቱ የተነሣ ጥቅሙን ማስጠበቅ ያልቻለ አካል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች የምንረዳው የወያኔንና የሸአቢያን በጣም የተራራቀና የማይመጣጠን የብቃትና የችሎታን አቅም ነው፡፡ እንደምናስበውና ከየዋሀን ወገኖቻችን ከወያኔ ቅጥረኞችና ካድሬዎች በሰፊው እንደሚወራልን ሸአቢያ ከወያኔ የላቀ የበለጠ መሠሪ ሸረኛ ብቃትና ችሎታ ያለው ቢሆን ኖሮ አይደለም ከወያኔ በበለጠ በተሸለ በምዕራባዊያኑ ተመራጭ ተፈላጊ ሊያደርገው የሚችሉ ነገሮች እያሉት ቀርቶ ባይኖረውም እንኳ የበላይነቱን ይዞ ልናየው በቻልን ነበር፡፡ የሆነው ግን የተገላቢጦሹ ነው ስልታዊ ጠቀሜታ እንደሌለውና በድንበር ኮሚሽኑ እንደተሸነፈ ሆኖ ከዓለም ዓቀፉም ኅብረተሰብ ተነጥሎ ተገልሎ ይሄ ሳያንሰው ማዕቀብ ተጥሎበት በማዕቀብ እየታሸ ለመኖር የተገደደ መሆኑ ነው፡፡
እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ምናልባት ሸአቢያ ምዕራባዊያኑን ከጎኑ ሊያሰልፍ የሚችልበት ጥቅም እያለው ምዕራባዊያኑ ከሸአቢያ ጎን ሊቆሙ ያልቻሉበትና ከወያኔ ጎን ሊቆሙ የቻሉበት ምክንያት “ወያኔ አልሸባብን አጥፍቶ ሱማሌን የተረጋጋችና መንግሥት ያላት ሀገር እንዲያደርግላቸው ስለሚፈልጉ እዚያ ላላቸው ጥቅም ወያኔን ስለሚፈልጉት ነው” የሚሉ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እውነት እንነጋገር ከተባለ የምዕራባዊያኑ ፍላጎትና ጥቅም እውን ሶማሊያ የተረጋጋች ሀገር እንድትሆን ነው ወይ? እንዳልሆነ ሊቢያ ላይ ምን ብለው ምን አድርገዋቸው እንደቀሩ የታየውና የምናውቀው ነው፡፡ አፈራርሰዋት የአሸባሪዎች መፈንጫ አድርገዋት ቀሩ እንጅ ቃል የገቡትን የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ ሰጥተው መስፍነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) መንግሥት እንዲመሠርቱ ሲረዷቸው ፈጽሞ አልታዩም፡፡ በመሆኑም የምእራባዊያኑ ጥቅምና ፍላጎት ሶማልያን ማረጋጋትና ባለመንግሥት ማድረግ ሆኖ ባሕረ ምድር ካላት ስልታዊ ጠቀሜታነት አንጻር ከሷ ሊያገኙት የሚችሉት ጥቅም ወያኔ ሱማሌ ላይ ከሚሰጣቸው ጥቅም በልጦባቸው አይደለም ከሸአቢያ ይልቅ ወያኔ በልጦባቸው ከወያኔ ጋር ሊቆሙ የቻሉት፡፡
እናም አትጠራጠሩ የከፋው የባሰው የላቀው መሠሪ ሸረኛና ሴረኛ ወያኔ እንጅ ሸአቢያ አይደለም፡፡ ሸአቢያ እንኳንና ፈጥሮ ፈልስፎ አሲሮ ጥቅሙን ሊያስጠብቅ ይቅርና በያዘው ጥቅሙን ሊያስጠብቅ የሚያስችሉትን ዕድሎች በመጠቀም ሌላው ቀርቶ ያንተ ነው የተባለለትን ውሳኔ ጥቅሙን ማስጠበቅ ያልቻለ ምስኪን ተሸናፊ ነው፡፡ ይህ ነገር ስለ ሸአቢያ መጥፎነት የመሠሪነት ብቃትና ችሎታ ሲወሩ ሲነገሩን የነበሩ ነገሮች ሁሉ እውነትነታቸውን እንደገና መለስ ብለን እንድናይ እንድንፈትሽ የሚያስገድደን ይመስለኛል ይገባልም፡፡ ቢያንስ የተባለው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ይመስለኛል፡፡ ጥቂቱ እንኳ እውነት ሊሆን ቢችል አስቀድሜ እንደገለጽኩት ለምን እንዴት ብሎ መጠየቅ ድርጊቱንም ማውገዝ ተገቢ ቢሆንም ከነበሩ የጦርነት ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር በምንም ተአምር መፈጸም አልነበረበትም ማለቱና በዚህም ላይ ተመሥርቶ የመጨረሻ ድምዳሜ ላይ መድረሱ ግን እጅግ እጅግ የዋህነትና እጅግም አለመብሰል ነው፡፡ በቤተሰብ መሀከል በጥቅም ምክንያት ወንድም በወንድሙ እኅት በእኅቷ ወንድም በእኅቱ ልጆች በወላጆቻቸው ወላጅ በልጆቹ ክህደት እየፈጸመ በሚባላበት ዘመን ጠላት ተደራርገው አንዱ ሌላውን ለማጥፋት በሚታገል በታጠቀ ሠራዊት መሀከል አንዳንድ ነገሮች መፈጸማቸው አይቀርምና ይሄና ያ እንዴት ለምን ማለትና ምንም ነገር እንዲፈጸም አለመጠበቅ ያንን የተፈጸመውን ጉዳይም የነገሮች መጨረሻ አድርጎ መቁጠር አሁንም እላቹሀለሁ እጅግ የዋህነትና አለመብሰል ነው፡፡ ምን ነካቹህ እቃቃ ስናጫወት እኮ አይደለም የኖርነው በጦርነት እሳት ስንለባለብ እንጅ፡፡ በፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ የሚታየው ዛሬ እንጅ ትላንት አይደለም በዓለማችን ትላንት ሲባሉ ሲቧጨቁ ሲጠፋፉ የነበሩ ዛሬ ላይ ግን እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ የገቡ በርካታ ሀገራትንና ቡድኖችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
የሆነ ሆኖ ይሄንን ሁሉ እንዳለ ተውትና ያልገባቸው ወገኖችም ሆኑ ወያኔ የገዛቸው ቅጥረኞች የሚናገሩት ክስ አንድም ሳይቀር ሁሉም እውነት እንደሆነ እንቁጠረውና ለወያኔ ከተገዙትና ከወያኔ ካድሬዎች በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወያኔ የተገዙና የወያኔ ካድሬዎች የሚያወሩትን ሳይሰማ ትግሉን ተቀላቅሎ ለድል የሚበቃበትን መንገድ ስናገር የሚከተለውን ይመስላል፡- የነጻነት ትግል ማለት ምንም ዓይነት መሰናክልና የፈተና ዓይነት እንቅፋት የሚያግደው የሚያደናቅፈው የሚገታው እንዲያግደው እንዲገታው እንዲያደናቅፈውም የማይፈቅድ ሁልጊዜም በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሳይሆን ባልተመቻቸና እንቅፋት መሰናክሎች ፈተናዎች በበዙበት ሁኔታ የሚደረግ የማይመቹ ሁኔታዎች ስላሉ በፍጹም ከመደረግ የማይቆም የማይቀር፤ ያለው ዕድል ከጠጉር የቀጠነ ዕድልም እንኳ ቢሆን በከፍተኛ ጽናት ትዕግሥትና ብልጠት እሱን ተጠቅሞ ዓላማውን ለማሳካት ከፍተኛ ትግልና ትንቅንቅ የሚደረግበት ሌላው ቀርቶ ምንም ዓይነት ዕድልም እንኳ ባይኖር ራሱን ዕድሉን ፈጥሮ ግቡን ለማሳካት የሚደረግ መራራ ትግል እንጅ እንደ ሽርሽር ምቹ ሁኔታዎች የሚጠበቁበት የትግል ዓይነት አይደለም፡፡
እናም አኔ የምላቹህ የወያኔ ቅጥረኞችና ካድሬዎች እንደሚያወሩት ሸአቢያ ከወያኔ የከፋና የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ቢሆንም እንኳ ትግላችን የነጻነት ትግል በመሆኑና በምንም የሚመለስ ሊመለስም የሚገባ ባለመሆኑ እንኳንና ይሄንን ያህል ዕድል ተፈጥሮ ቀርቶ ምንም ዓይነት ዕድል ባይኖርም ራሱ ዋሽተን ወስልተን ቀጥፈን ሌሎች የብልጠት መንገዶችን ተጠቅመንም ቢሆን ዕድሉን ፈጥረን ግባችንን የማሳካት ግዴታ ያለብን በመሆኑ ሸአቢያ እንዳሉት ቢሆንም እንኳ ባለፈው ጊዜ እንዳልኳቹህ የልባችንን በልብ አድርገን መዋሸት ካለብን እየዋሸን “ቃል ግቡልኝ ፈርሙልኝ ማሉልኝ እንዲህ እንዲህ ታደርጉላኛላቹህ” ቢልም በፍጹም እንደማታደርጉት ልባቹህ እያወቀም አንኳ “እሽ ምን ችግር አለው! የፈለከውን እናደርጋለን! እኛ ሎሌህ ደጋፊዎችህ አጋሮችን ነን! ላንተ የማንሆነው የማናደርገው ነገር የለም!” እያልን ግጥም አድርገን በዐሥር ጣታችን በመፈረም እርኩስ ክፉ መሠሪ መሆኑን ብናውቅም “ደግ ቅንና ቅዱስ ነህ!” እያልን “ሸአቢያ ሽህ ዓመት ይንገሥ በሉ!” ቢል “ለምን ሽህ ዓመት ብቻ ለዘለዓለም ኑርልን!” እያልን ሥራችንን በመሥራት ይሄንን ክፉ ቀናችንን ዛሬን ተሻግረን ግባችንን አሳክተን ከነጻነቱ ቀን ነገ ላይ መድረስ ግድ ይለናል፡፡ ዕድል ባይኖርም ዕድል መፍጠር ይሉሀል ይሄ ነው፡፡ እንዲህ የምናደርገው ለምንድን ነው? እውነት ከሆነ ሸአቢያ የማይወደውን አቋም በመያዛችን በሸአቢያ እንዲጠፉ ተደርገዋል እንደተባሉት ወገኖች ከመጠቃት ለመዳን ነው፡፡ በዚህ የትግል ዘመን እውነት ብቻ ተናግረን ፈተናዎቻችንን ማለፍ መሻገር በፍጹም በፍጹም አንችልም፡፡ የልብን በልብ አድርገን ማስመሰልን መዋሸትን መቅጠፍን በሚገባ ልንካንበት ይገባናል ለምን ሲባል? ለዚህች ውድ ሀገራችንና ለውዱ ሕዝባችን ህልውናና ነጻነት ስንል፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ነገሩ የሚገባቹህ የሚገለጥላቹህ ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም ወያኔ ወይም የወያኔ ቅጥረኛ ካልሆንን በስተቀር ሀገራችንን የምንወድ የሀገራችንንና የሕዝባችንን ነጻነት ፈላጊ ሆነን ከዚህ ሕዝባዊ ትግል ልንሸሽ ጭራሽም ትግሉት ልንቃወም የምንችልበት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ በሚገባ በመረዳት እያንዳንዳችን እንደየችሎታችን ትግሉን በመደገፍ የትግሉ አካል መሆን አማራጭ የሌለው መሆኑን አውቀን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡
  1. “የታጠቀ ኃይል የምንፈልገውን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፣ በአፈሙዝ የሚገኝ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) የለም፣ የታጠቀ ኃይል የራሱን እንጅ የሕዝብን ፍላጎት አያሟላም፡፡ ከሚል ዓለም አቀፋዊውን ነባራዊ ሁኔታ ካልተገነዘበ አስተሳሰብ” ይህ የሥጋት ሐሳብ ላይ ላዩን ሲያዩት እውነት ይመስላል፡፡ በተለይ ደግሞ ምሳሌ ይሉና ደርግንና ወያኔን ምሳሌ አድርገው ሲያቀርቡ እውነት ይመስላቹሀል፡፡ ትንሽ ልትጠረጥሩ የምትችሉት “ታዲያ ምን ይሻላል?” ብላቹህ ስትጠይቋቸው መልስ ሲያጡ ወይም የሚሰጡት መልስ አጥጋቢ ያልሆነና ወያኔን የሚጠቅም ሆኖ ስታገኙት ነው፡፡ ምናልባት እነኝህ ቅጥረኞች የሚያነሡትን ይሄንን የሥጋት ሐሳብ የሚያነሡ ሌሎች የዋሀን የሕዝብ ወገኖች ካሉ ለነሱ ላነሣው የምፈልገው ጥያቄ ቢኖር፡- ይሄንን የሚሉ ሰዎች ለሀገርና ለሕዝብ ታማኝ ከሆኑና ይሄንን ቅን ዓላማቸውን ይዘው የሚታገሉ ከሆነ ወያኔን አባራሪዎቹና እንደተመኙት ሁሉ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት የሚያደርጉት እነሱው አይደሉም ወይ? ሌላ ከማርስ የሚመጣ አብሯቸው የሚገባና አንባገነን ካልሆናቹህ ብሎ የሚያስገድዳቸው አካል አለ ወይ? ዋናው የዓላማ ጽናትና ታማኝነት ነው እንጅ መሣሪያው አይደለም፡፡ ታማኝ ያልሆነ ግለሰብ ወይም አካል ካለ ሲቪል (ሕዝባዊ) ሆኖም ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም በተጻራሪ በመቆም ሕዝብን የሚጨቁን የራሱን ወይም የቡድኑን ጥቅም የሚያስጠብቅ ለራሱና ለቡድኑ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ ከመሆን እንደማይድን የብዙ ሀገራት ተሞክሮ በሚገባ ያሳየናል፡፡
በዓለማችን በጦር ኃይል የተመሠረቱ መንግሥታት አንባገነን የሆኑ እንዳሉ ሁሉ የተደላደለ ሕዝባዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መንግሥት እንዲመሠረት እንዲፈጠር ያደረጉም አሉ፡፡ ዋናው የዓላማ ጽናትና ታማኝነቱ ነው፡፡ በዚህ ላይ አርበኞች ግንት 7 ዓላማው ምን እንደሆነ በግልጽ አስታውቋል “የምታገለው ሕዝብ የፈለገውን የወደደውን መሾም ያልፈለገውን ያልወደደውን መሻር የሚችልበት ሥልጣን እንዲኖረው የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ነው እንጅ ወያኔን አውርጀ ሥልጣን ለመያዝ አይደለም፡፡ ወያኔን ደምስሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ የፈለገውን የወደደውን መርጦ መንግሥት ያቋቋመ የመሠተረ ጊዜ የኛ ትግል ይጠናቀቃል” በማለት፡፡ ስለሆነም እንግዲህ እውነተኛ የሕዝብ ልጅ ካለ ለግል ጥቅም ለሥልጣን ሳይሆን ለዚህች ሀገርና ለሕዝቧ ነጻነት ለፍትሕ ለእኩልነት እታገላለሁ የሚል ካለ ቦታው አርበኞች ግንቦት 7 ነው ሔደህ ግባ፡፡
እንዲያው ነገሩን አልን እንጅ እውነተኛና ትክክለኛ ለራሱ ቡድናዊና ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ሳይሆን ለሕዝብ የታመነ ኃይል ታግሎ መጥቶ ይሄንን ማድረግ ቢችልና ሕዝብ የወደድከውን የፈለከውን ምረጥ ተብሎ ሙሉ መብት ቢሰጠው ከባድ መሥዋዕትነት ከፍሎ ለዚህ ክብር ያበቃውን፣ ነጻነት ያቀዳጀውን፣ የሥልጣን ባለቤት ያደረገውን፣ ለሀገሩና ለወገኑ እስከ ሞት ድረስ ራሱን የሰጠለትን ትቶ እዚህ ከሞቀ ቤቱ ቁጭ ብሎ ሲያበግነው የኖረውን፣ እንቅፋት እንኳን እንዳይመታው እራሱን ሲጠብቅ የኖረውን፣ ከሕሕብና ከሀገር ይልቅ ራሱን የሚወደውን እራሱን የሚያስቀድመውን፣ ለሕዝብና ለሀገር ሲል ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል የማይፈቅደውን፣ ድፍረት ቁርጠኝነት ጽናት የሌለውን፣ ታማኝነቱን ሀገር ወዳድነቱን ከወሬ ባለፈ በተግባር መሥዋዕትነትን እስከመክፈል ድረስ ታምኖ ዋጋ ከፍሎ ማሳየት የማይችለውን፣ የጭርታ የሰላም ጊዜ አርበኛ ተሽታሻ ተሸታሻውን የሚመርጥ ይመስላቹሀል? በፍጹም!
ወያኔ እኮ መሥዋዕትነትን እንደመክፈሉ እስከዛሬ ድረስ በተደረጉት 5 “ምርጫዎች” በኢትዮጵያ ሕዝብ ሊመረጥ ያልቻለው እኮ ወያኔ ካፈጣጠሩ ኢትዮጵያዊ ባለመሆኑ፣ ዓላማና አስተሳሰቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሽዎች ዓመታት የገነባው የታሪኩ የአንድነቱ የማንነቱ የሥልጣኔው የእሴቶቹ ጠላት ሆኖ ከሚያውቀውና ከሚያምንበት በተጻራሪ ቆሞ ታሪኩን በማጉደፉ፣ ለማፈራረስ ጥረት በማድረጉ፣ በስንት ድካም የገነባውን አንድነቱን ጨርሶ ለማጥፋት በዘር በሃይማኖት እየከፋፈለ ለማባላት በመጣጣሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተናቀ ተጠላ፤ ከትግሬና ከትግራይ ውጪ ኢትዮጵያን ለማየት ለማሰብ የሚችልበት አቅም አልባ በመሆኑ፣ አስተሳሰቡ ዓላማው ሩጫው ሁሉ ጎጠኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር ሥዕል በጭንቅላቱ የሌለች ከሌሎቻችን ልቦናም እንድትጠፋ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ጭራሽም ሊያፈራርሳት ነገር የሚያሴር ክፋት የሚሸርብ በመሆኑ፣ ባጠቃላይ ለታሪኳ ለማንነቷ ለሥልጣኔዋ ለእሴቶቿ ሁሉ ጠላት በመሆኑ የሀገር ክህደት በመፈጸም ከመሬቷ ጀምሮ ሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞቿን አሳልፎ የሚሰጥ የጠላት ቅጥረኛና ባንዳ በመሆኑ ለመንግሥትነት አይደለም ለዕድር አሥተዳዳሪነት እንኳን የሚበቃ አቅም ብቃት ችሎታ ቅንነት የኃላፊነት ታማኝነት ተጠያቂነት ግልጽነት ዕውቀት ተወዳጅነት የሌለው የወንበዴ ጥርቅም ስለሆነበት እንጅ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ቆርጠው እንደመታገላቸውማ ቢሆን ማጭበርበር ማስገደድ ማስጨነቅ ማወናበድ ሳያስፈልጋቸው ዕድሜ ልኩን ያለ እነሱ የሚመርጠው ባልነበረ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሕዝብ የሚወደውን እስከ ሞት ድረስ የሚታመንለትን ዋጋ የሚከፍልለትን የሚያከብረውን ይወዳልና፡፡ እሱም በተራው የመጨረሻውን ክብር ሰጥቶ ያከብራልና፡፡ የዛኑ ያሕል ደግሞ እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕትነትን ለመክፈል የታመነ ቢሆንም እንኳ እንደወያኔ ሁሉ ለጥፋትና ለወረደ ለጠባብ የጥፋት ዓላማ መሥዋዕትነትን የከፈለ ሲያጋጥመው እጅግ ይንቃል ይጠላል ያወግዛል ይረግማል ያገላል ያዋርዳል ይጸየፋል ያንቋሽሻል ያበሻቅጣል እንደ መርገም ጨርቅ ይመለከታል፡፡
  1. “በዘመነ ደርግ ወያኔና ሸአቢያ ደርግን ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የስንቅና ትጥቅ (logistics) ሌላም ድጋፍ ያደርጉላቸው እንደነበሩ ሀገራትና አንዳንድ አካላት በዚህ ዘመን ለእኛ ሊያደርግልን የሚችል ባለመኖሩ በቂ ስንቅና ትጥቅ ሊገኝ ስለማይችል ከንቱ ድካምና ከንቱ መሥዋዕትነት ነው” ለሚለው፡- እርግጥ ነው በዚያን ዘመን ወያኔና ሸአቢያ ሲያገኙት የነበረውን ዓይነት ድጋፍ ከእነኛው ሀገራት ማግኘት አንችል ይሆናል፡፡ ይሁንና በዚህ በኩል ያለውን ክፍተት ሸአቢያ ጦርነቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን የራሱም መሆኑን በሚገባ ስለሚያውቅ ከምንም በላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወያኔ ነጥለው አርቀው ብቻውን ማስቀረት የሚችሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ከጎናቸው ማሰለፍ የሚችሉ እንዲህ ዓይነት አጋዥ ኃይል ማግኘቱን ቢሳልም የማያገኘው ወርቃማ ዕድል መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በስንቅና ትጥቅ በኩል ያለውን ክፍተት ሸአቢያ ለእኛ ብሎ ሳይሆን ለራሱ ብሎ የሚያደርገው የሚያቀርበው በመሆኑ ይሄ የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም፡፡ እነ አቶ ኢሳይያስ በግልጽ እንዳስታወቁት “ላደረኩላቹህና ለማደርግላቹህ ድጋፍ ምንም ዓይነት ምላሽ አልፈልግም የተረጋጋች የበለጸገች እኩልነትና ፍትሕ የሰፈነባት ሰላማዊት ኢትዮጵያን ብሎብ የተረጋጋና ሰላማዊ የቀጠናው ሀገራት እንዲኖሩ ካለኝ ጽኑ ዓላማ ያደረኩትና የማደርገውም በመሆኑ” በማለት ያስታወቁና ለመካስም ካላቸው በጎና ቁርጠኛ አቋም በመነሣት የተዋሐደችና ጠንካራ ምሥራቅ አፍሪካን ለመፍጠር ካላቸው የተቀደሰና ታላቅ ርእይ አንጻር ይሄንን ለማሳካት ያስችል ዘንድ መሠራት ያለባቸውን ሥራዎች እየሠሩ እንደሆነ አምነው ታሪክ ሠርቶ ለማለፍ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ዓላማቸውን ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ አቅድ አኳያ ግልጽ ያደረጉ በመሆኑ “እነ አቶ ኢሳይያስ ለዚህ ሁሉ ውለታ ምላሽ ሳይፈልጉ ይሄንን ሁሉ ነገር ሊያደርጉልን አይችሉም ላደረጉትና ለሚያደርጉት ምን ልንመልስ ምን ልንከፍል ነው?” የሚያስብልና የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሁላችንም መወጣት ያለብንን ግዴታና ኃላፊነት የሚጠበቅብንንና ማድረግ ያለብንን ሥራ ነው እየሠራን ያለነው፡፡
ይሁን እንጅ ለሀገራችንና ለሕዝባችን በማሰብ ታጋይ ወገኖቻችን የማይሆን ውለታ (commitment) ውስጥ እንዳይገቡ የምንሠጋና እንዲገቡም የማንፈልግ ከሆነ ለእኛ ነጻነትና ጥቅም ሲሉ ሁለንተናቸውን አሳልፈው የሰጡ እነሱ እንኳን እንዳሉ በማሰብ እያንዳንዳችን ከተረፈን ሳይሆን ምቾታችንን ቆጠብ በማድረግ “ለእኛ ይቅርብን! እኛን ይቸግረን!” ብለንም ቢሆን ትርጉም ያለው ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በወሬና ከንፈር በመምጠጥ ወይም በማጨብጨብ ብቻ የሚገነባ የሚሠራ ምንም ነገር የለም፡፡ ተግባር ያስፈልጋል ሀገርን መውደድ በተግባር ከምናደርገው አንዳች ነገር ውጭ በምንም ሊገለጽ አይችልም፡፡ ይሄንን ማድረግ ሳይችል ወሬ ብቻ የሚያወራ ካለን ሊያመጣው የሚችለው ለውጥ ካለመኖሩም በላይ ለወያኔ ዕድሜ መርዘም የራሱን እገዛ በማበርከቱ በሀገር ላይ የሚደርሰው ጉዳትና ኪሳራ ከወያኔ በማይተናነስ መልኩ በታሪክ ተጠያቂ እንደሆንን ልንገነዘብ ይገባል፡፡
በተለይ በተለይ ሀገር ብዙ ወጪ አውጥታባቹህ ሳይማር አስተምሮ ተቸግሮ አሳድጎ ነገር ግን በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች (push factors) ከሀገራቹህ ተሰዳቹህ እናንተ እዚህ እንድትደርሱ ሽራፊ ሳንቲም ያላወጣባቹህን የባዕድ ሕዝብና የባዕድ ሀገር በማገልገላቹህ ሀገራቹህን ሕዝባቹህን ባለማገልገላቹህ ውለታውን ለመክፈል ባለመቻላቹህ ቁጭት የሚያንገበግባቹህ የሚቆጫቹህ የሚከነክናቹህ ዕረፍት የነሳቹህ ወገኖች ካላቹህ በተለያየ ምክንያት በረሀ ወርዳቹህ ትግሉን በአካል መቀላቀን ባትችሉም ለዚህ ሕዝባዊ ትግል ትርጉም ያለው ድጋፍ በማድረግ ሀገርራቹህን ልታገለግሉ ባለመቻላቹህ የተሰማቹህን ቁጭት ጸጸት በዚህ መወጣትና ሀገር ወገናቹህን መካስ እንደምትችሉ እንዲሁም ደግሞ  ጉልበታቹህን ዕውቀታቹህን ችሎታቹህን በባዕድ ሀገራት በማፍሰስ ዕድሜያቹህን የፈጃቹህና በዕድሜ መግፋት ምክንያት ከዚህ በኋላ በዕውቀታቹህ በጉልበታቹህ በችሎታቹህ ሀገራቹህንና ሕዝባቹህን ማገልገል የማትችሉ ጡረተኛ ወገኖች ሁሉ ካፈራቹህት ካላቹህ ገንዘብና ንብረት ቁጭታቹህን ጸጸታቹህን ሊያስወግድላቹህ ሊያስወጣላቹህ የሚችል መጠን ያለውን ገንዘብ ለትግሉ በማበርከት መንፈሳዊ እርካታን እንድታገኙ ይንን አጋጣሚ እንድትጠቀሙበት ላመለክታቹህ እወዳለሁ፡፡
የሞቀ ቤታቸውን ቅንጡ ኑሯቸውን ከፍ ያለ ደረጃቸውን ሁለነገራቸውን ጥለው ለእኔና ለእናንተ ለሚወዷት ሀገራቸው ሲሉ ነፍሳቸውን እስከመስጠት ታምነውና ቆርጠው በረሀ የገቡ ፕሮፌሰር ዶክተር ኢንጂኒየር… ወገኖቻችን ግንባር በግንባር ተፋጠው ዕላያቸው ላይ የሚወርድባቸውን ዝናብና ፀሐይ ሳይማረሩ ከሞት ጋር ተፋጠው ለማሸለብ ፋታ አጥተው ያገኟትን ተቃምሰው በረሀብ እየተፈተኑ እነኝህንና ሌሎችንም ሁሉ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ መሆናቸውን እያወቃቹህ ከሞቀ ቤታቹህ ሆናቹህ ይህንን ማድረግ ይከብዳቹሀል ለማለት እጅግ ይከብደኛል፡፡
  1. “ሸአቢያ እኛን ይዞ ወያኔን ለማስፈራራትና ከወያኔ የሚፈልገውን ለማግኘት እንጅ የምናደርገው ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ለስኬት እንዲበቃም በፍጹም አይፈልግም” ይሄንን የሚሉ ሰዎች ምን ይጠቅሳሉ ለምሳሌ ይሉና “የአርበኞች ግንባር ትግል ከጀመረ 16 ዓመታት ሆኖታል፡፡ ይሄንን ሁሉ ዓመታት ሲቆይ አንድም የሚጠቀስ ተግባር ለመፈጸም አልቻለም እንዲዋጋ አልተፈቀደለትም ዝም ብለው ነው እንዲቀመጡ ያደረጋቸው” ይላሉ፡፡ ይመስለኛል እንዲህ እንዲሉ ያደረጋቸው ስለትግል ስለጦርነት በቂ ግንዛቤ አለመያዛቸው ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ውጤት ያለው ጦርነትም ሆነ ሽምቅ ውጊያ በቂ ኃይል ሳይያዝ፣ በቅጡ ሳይደራጁ፣ ሕዝባዊ ዕውቅናና ድጋፍ በበቂ ደረጃ ሳይገኝ ማድረግ ታይቶ ለመጥፋት ካሆነ በስተቀር ዘለቄታ ያለው እንቅስቃሴ ለማድረግ አይቻልም፡፡ ይሄንን ቅሬታ እንደሚያነሡ ሰዎች አስተሳሰብ ቢሆን ኖሮ የአርበኞች ግንባር ባለው አነስተኛ ኃይል እንደተመሠረተ ተንቀሳቅሶ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ጠፍቶ ነበር፡፡ እንደሚመስለኝ ሸአቢያም ይሄንን እንዳያደርጉ የከለከለበት ምክንያት የተጠናከረ ኃይል እስኪኖራቸው እስኪይዙ መኖራቸው መደራጀታቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በቂ ግንዛቤ እስኪያዝበት ድረስ መጠበቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ይሄንን ቅሬታ የሚያቀርቡ የትግሉ አካል የነበሩ አሁን ላይ በዚህ ቅሬታቸው ምክንያት ከዓመታት በፊት ትግሉን ጥለው የወጡ ግለሰቦች በወቅቱ ሸአቢያ ይሄንን ባለመፍቀዱ ያነሡበት ቅሬታ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ሸአቢያን በጣም በጥርጣሬ ዓይን ስለምናይ ብቻ እያንዳንዷን ነገር በክፋት እየተረጎምን ለተሳሳተ ድምዳሜዎች እየተዳረግን እንደሆነ ልብ ብንል መልካም ነው፡፡ ይህ ችግር በሥራችን ላይ የራሱ የሆነ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላልና በማስተዋል ብንራመድ መልካም ነው፡፡
አሳቢ የመሰሉ ወገኖች የሚሰጡትን ምክር ሐሳብና ተቃውሞ አሳቢ ሆነው ሳይሆን ወያኔ ገዝቷቸው ቅጥረኞች ስለሆኑ እንደሆነ በምን ልናውቅ እንችላለን?
ይሄን ለመለየት በተለይ በአሁኑ ጊዜ ብዙም የሚያስቸግር አይመስለኝም ለማንኛውም እነኝህ ነጥቦች ይጠቅማሉ ብየ አስባለሁ፡-
  1. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ አኳያ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሀገርንና ሕዝብን ሳይሆን ወያኔን የሚጠቅም ከሆነ፡፡
  2. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ትግሉን ወደኋላ ለመሳብ ለማሰናከል የሚያሴር ከሆነ፡፡
  3. አሳቢ መስለው እኩይ ሥራቸው የሚከውኑት ወሳኝና አንገብጋቢ ወቅትን (timing) እያዩ ከሆነ ማለትም ወያኔ ሥጋት በተጋረጠበት ሰዓትና አጋጣሚዎች ላይ ከሆነ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አርበኞችና ግንቦት ሰባት ውሕደት በፈጸሙ ወቅት፣ ሰሞኑን ማጥቃት በመጀመሩ ትግሉን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ወሳኝ ወሳኝ ምእራፎች በሚመዘገብበት ወቅቶች ላይ ማለት ነው እነኝህ ቅጥረኞችም ይሄንን እመርታ ሊቀለብስ የሚችል ሥራን በመሥራት እራሳቸውን ጠምደው ታይተዋል፡፡
  4. እነዚህ አሳቢ መስለው የቀርቡ ግለሰቦች ሕዝባችን ነጻ እንዲወጣ የሚያቀርቡት ተጨባጭና ጠቃሚ አማራጭ የሌለ መሆኑና “ዝም ብለን አርፈን በወያኔ መገዛት ነው የሚሻለን” የሚል ዓይነት ከሆነ፡፡
እነዚህ እነዚህ ነጥቦች ቅጥረኞችን ለመለየት ይጠቅማሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ እነዚህ ኅሊናቸውን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናቸውን ለሆዳቸው የሸጡ ምንደኛ ግለሰቦች ለወያኔ ያደሩ ሳይመስሉ መርዘኛ ሐሳቦቻቸውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ በነጻነት ለመናገር ለመጻፍ የሚጠቀሙበት አንድ ሽፋን አለ “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ከመጠቀምና ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ” በሚል ሽፋን ነው፡፡ እንዳሉትም በትክክል ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽና ይሄንን ዲሞክራሲያዊ መብት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ከሚል አንጻር ያደረጉት ከሆነ ሚዛናዊነትን ሲጠብቁ ከሁለቱም አቅጣጫዎች ጠንካራ ጠንካራ ሐሳቦችን ሲያስተናግዱ ታገኟቸዋላቹህ፡፡ ነገር ግን ከሁለቱም አቅጣጫዎች ያሉ ጠንካራ ጠንካራ የመከራከሪያ ሐሳቦችንና ተሟጋቾችን የማያስተናግዱና ሚዛናዊነትንም የማይጠብቁ ወያኔን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ ወገን የማድላት ዝንባሌ የሚታይባቸው ከሆነ ይሄንን “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ተግባራዊ ከማድረግ” የሚለውን መብት ሥውር ተልእኮዋቸውን ለማሳካት ለሽፋን እየተጠቀሙበት ነውና ቅጥረኞች መሆናቸውን ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡
ለምሳሌ የቪኦኤው “ጋዜጠኛ” ሔኖክ ሰማእግዜር አቶ ኃይለማርያም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ሊያገኙት ስለነበረውና በተቃውሞ ምክንያት እንዳያገኙ የተደረገውን ሽልማትና እውቅና ዘገባ በሠራበት ጊዜ ዘገባውን የሠራበት መንገድ ግልጽ በመሆኑ ማንነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ሆን ብሎ የጋዜጠኝነትን መርሖዎች ግልጽነትንና ሚዛናዊነትን ባለመጠበቅ ወያኔን ለመጥቀም በማሰብ ትክክለኛ መረጃወች እንዳይካተቱ በማድረግ ዕውነትን ያዛባ ዘገባ ሠርቷል፡፡
ይህ ሰው ይሄንን ዐይን ያወጣ ስሕተት ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ቦይንግ 767 የመንገደኞች አውሮፕላንን (በረርትን) በመጥለፍ አውሮፓ ጥገኝነት የጠየቀበትን ዘገባም በተከታታይ በሠራበት ወቅት ወያኔ “አብራሪው ለረጅም ጊዜ የአእምሮ ጭንቀት ላይ ነበረ ይሄንን ያደረገው ሕመሙ ተባብሶበት ከዚህ ችግሩ የተነሣ ነው” ብሎ የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለመሸፋፈን ጥረት በማድረግ የሰጠውን ሐሰተኛ ስም አጥፊ መግለጫ እውነት ወይም ትክክለኛ ለማስመሰል በማሰብ አሁንም ሚዛናዊነትን ያልጠበቀና የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ የጣሩ ዝግጅቶችን አቅርቦ ነበር፡፡ እናም ማንም ጋዜጠኞችም ሆኑ የብዙኃን መገናኛዎች ግልጽ የሆኑ የሞያዊ አሠራር ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ስታዩ ያ ሰው ወያም ያ አካል ለሚከላከልለት ሀቁን ለደበቀለት (ለወያኔ) ያደረ የተገዛ የሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጥር እንደሆነ ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡ እንዲህ መሆኑ በግልጽ የታወቀ ሰው በዚያ የጥፋት ዲርጊቱ ቢገለልና ቢወገዝ ተወገዝኩ ተገለልኩ ጥቃት ደረሰብኝ ብሎ ሊከስ ሊያማርር ሊወቅስ አይችልም መብትም የለውም፡፡
ምክንያቱም ጉዳይ ከሞያዊ ግድፈት አልፎ ሞያውን በማርከስ ኃላፊነትና ግዴታውንም ለግል ዓላማውና ጉዳዩ በመተላለፍ ሞያው የጣለበትን ኃላፊነት አላግባብ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በመጠቀም ማለትም ወያኔ ወይም የወያኔ አባል በመሆኑ ሆን ብሎ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ በመሞከር ጉዳዩን ወደ የመደብ ትግል ፍትጊያ አሻግሮታልና ወይም እንዲለወጥ ያደረገ በመሆኑና የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በወያኔ ላይ ተስፋ ቆርጦ ትጥቅ ያነሣበት ሁኔታ ላይ ያለ በመሆኑ ይህ ሰው ከመወገዝም አልፎ ቦታና ሁኔታዎች ቢፈቅዱና እርምጃ ቢወሰድበትም እንኳ ድርጊቱ ሕገ ወጥ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ ምክንያቱም በጋዜጠኝነቱ ያለውን ከለላ በሠራው ወንጀል አጥቶታልና፤ እራሱን ከጋዜጠኝነት አውጥቶ እንደ አንድ የወያኔ ታጋይ ሁሉ የወያኔ ጥቅም አስከባሪ አድርጓልና፡፡
ይህ እርምጃ ቢወሰድበት “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር! እያሉ እነሱ ራሳቸው ይሄንን የሚያደርግን ሰው ያጠቃሉ” ተብሎ ሊገለጽ በፍጹም በፍጹም አይደባም፡፡ ይሄ ብየና አለመብሰልና አለማገናዘብም ነው፡፡ ምክንያቱም የሰውየው ሥራ ሆን ብሎ ከሞያዊ ሥነምግባሩ ውጭ በፈጸመው ስሕተት ምክንያት ሐሳብን በነጻ ከመግለጽ ጋራ ምንም የሚያገናኘው ነገር የሌለ በመሆኑና ይህ የፈጸመው ስሕተትም እራሱን እንደ አንድ የወያኔ ወታደር አድርጎ ስላቆመ ያለውን የጋዜጠኝነትም ሆነ የሌላ መብት ከለላውን ስለሚያሳጣው፡፡ ይህ ሰው ሚዛናዊነትንና ከሁለቱም ወገኖች ጠንካራ የሆኑትን ሐሳቦች ለማስተናገድ የፈቀደ ባለመሆኑ ይልቁንም ትክክለኛ መረጃዎችን ሆን ብሎ የሰወረ በመሆኑ ሐሳብን በነጻ የመግልጽ መብትን ለቅጥፈቱ ሽፋን ሊያደርግ ስለማይችል፡፡
ይሄ “ጋዜጠኛ” ሆነ ሌላ ማንነቱ የታወቀ ሰው ኢትዮጵያዊያን በሚያደርጉት ማንኛውም ኩነት ተገኝቶ ልዘግብ ቢልና ሕዝብ የሚያውቀው በወያኔነቱ በመሆኑ ከወያኔ ጋርም ልዩነታችንን በውይይትና በሌሎች ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መንገዶች ልንፈታ የምንችልበት መንደግ ዕድል ተጠርቆሞ የተዘጋ በመሆኑና በቀረልን ብቸኛ አማራጭ በኃይል እርምጃ ለመፍታት መብታችንን ለማስከበር የተገደድንበት ሁኔታ ውስጥ ያለን በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ሕዝቡ በራሱ ዝግጅቶች እንዳይገኝ የመከልከል የማስወገድ መብት አለው፡፡
“እነዚህ የሚከለከሉ (ከዚህ ዞር በሉልን አንያቹህ!) የተባሉ ጋዜጠኛም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች የወያኔ ደጋፊ ወይም ወያኔ እንኳን ቢሆኑ በመነጋገር ነው እንጅ ልዩነቱ መፈታት ያለበት ለምን በኃይል ይሆናል?” ከተባለ በመነጋገር ልዩነትን ለመፍታት 24 ዓመታት ለምነን ተማጽነን አይሆንም አይቻልም ተብለን መብታችንን ተነጥቀን ተነጋግሮ ልዩነትን የመፍቻው ዘመን አልፎ ሳንወድ በግድ ተገፍተን ወደ ሌላኛው የተተወልን ብቸኛ አማራጭ ማለትም በትጥቅ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነትና መብት የማስከበር አማራጭ የገባንበት ወቅት ውስጥ በመሆናችን እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ካጠገባችን እንዳይደርሱ መከልከል ማራቅ እንችላለን መብታችንም ነው፡፡ ሌላ እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ ያሉበት ሀገር ሕግና ሁኔታዎች አይፈቅዱም እንጅ እንደጠላትነታቸው ሁሉ ሁሉንም ዓይነት እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ የያዝነውና የገባንበት ሕዝባዊ ትግል ያስገድደናል፡፡
ሌሎችም ድረ ገጾችና የብዙኃን መገናኛዎችም ቢሆኑ የመጻፍ፣ የመናገር፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሲባል የሕዝብን የጋራ ጥቅም የሀገር ደኅንነትንና ህልውናን ለመጠበቅ ለመንከባከብ የተለየ ሐሳብ ካለ እሱን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት እንጅ ሀገርንና ወገንን የሚጎዳ ወይም ሀገርንና ወገንን የሚጎዳን አካል ጥቅም ለመጠበቅ የሚነገር የሚጻፍ ሐሳብን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት አይደለም፡፡ በግልጽ አማርኛ ወያኔ የዚህች ሀገርና የሕዝቧ ቀንደኛ ጠላት እንደመሆኑ ማንም ሰው የወያኔ ቅጥረኛ ሆኖ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ማለትም ከድሮ ጀምሮ የራሱን ቡድናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሀገርን ሕልውናንና የሕዝብን ደኅንነትና ጥቅሞች ለመጉዳት ለማጥቃት ለአደጋ ለመዳረግ የሚያሴረውን የወያኔን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የተሰጠ መብት አይደለምና በዚህ ሽፋን ይሄንን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል፡፡ የትም ሀገር ቢሆን ያለው አሠራር ይህ ነው፡፡ አሜሪካም ብትሆን ዜጋዋ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ሥራ ሠርቶ “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው” ቢል አትሰማውም “ብሔራዊ ጥቅሜን ለአደጋ ዳርጓል የሀገርንና የሕዝብት ደኅንነት ለአደጋ አጋልጧል ወይም ለጠላት ተቀጥሮ በመሥራት” ወንጂላ እንደ ስኖውደን ታሳድደዋለች እንጅ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው ብላ አትምረውም፡፡
እነኝህ አካላት ሞያዊ ሥነምግባራቸውን በመጣስ የሀገራችንን ጠላት የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ከወያኔ ጋር በማበር የወያኔ ቅጥረኛ በመሆን መረጃን በማዛባት እንደሚንቀሳቀሱ ባወቅን ጊዜ ይሄንን መብት አጥተዋልና ይሄንን መብት ለሽፋን መጠቀም አይችሉም፡፡ አሜሪካ ጥቅሟን የሚጎዳባትን ሰውና ዘገባ የሀገርና የሕዝብ ጠላት አድርጋ እንደፈረጀችና እንደምታሳድድ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያዊያንም የሀገራችንንና የሕዝባችንን ብሔራዊ ጥቅሞች የሕልውናችንና የደኅንነታችን ጠላት የሆነው ወያኔን ያገለገለ ወይም የደገፈ ጋዜጠኛንም ሆነ ማንኛውንም ሌላ አካል ሁሉ የሀገራችንና የሕዝባችን ጠላት እንፈርጃለን እናሳድዳለንም፡፡ በግልጽ አማርኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ዕድሎች ተዘግተውበት መብቶቹን ለማስከበር ተገዶ የትጥቅ ትግል ውስጥ የገባበት ሁኔታ ውስጥ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ወዶና ፈቅዶ የወያኔ አባልና ደጋፊ የሆነ ካለ ይህ ሰው ሊሸሸግበትና ሊታደገው የሚችል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለው ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡
ይመስለኛል በሌላም በኩል ወይ ድፍረት ቁርጠኝነት አጥተው ይሁን ወይ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጡት ቤተሰባዊም ሆነ ሌላ ጉዳይ ኖሮባቸው ብቻ በአንድም በሌላም ምክንያት በትጥቅ ትግሉ መሳተፍ የማይችሉ ከመሆናቸውና የትግሉ አካል ካለመሆናቸው የተነሣም “የሚመጣው ለውጥ በግል እኔን አያካትተኝም በተዋናይነት ቦታ ሰጥቶ አያሳትፈኝም” ከሚል ሥጋትና “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ከሚል ለራሳቸውም ለወለዷቸው ልጆችም ለሀገር ለወገንም ፈጽሞ የማይጠቅም የደነቆረና በሽተኛ የሆነ የራስወዳድነትና የምቀኝነት ጠንቀኛ አስተሳሰብ ወያኔ ወይም የወያኔ ደጋፊም ሳይሆኑ እየተደረገ ያለውን የትጥቅ ትግል የሚቃወሙ ወይም የማይደግፉ ያሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ የሚያስቡ ግለሰቦች የማሰብና የማገናዘብ ችሎታ በጣም የወረደ ነው፡፡ ከተቆጣጠራቸው ክፉ የምቀኝነት መንፈስ የተነሣ እንደ ዜጋ እራሳቸውን ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው አስመስጋኝና አስከባሪ ሥራ በሌሎች ሲደረግ ሲያዩ ዐይናቸው ደም ይለብሳል፡፡ ዜጋ እንደመሆናቸው የዜግነት ግዴታ እንዳለባቸው ተረድተው እንደ ዜጋ ለሀገሬ ምን ማበርከት ይጠበቅብኛል? ሀገሬ ወገኔ ከኔ ምን ይጠብቃሉ? ብለው ራሳቸውን በመጠየቅ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት አስበው በቅንነት ተንቀሳቅሰው የሚያውቁ አይደሉም፡፡ ከተንቀሳቀሱም ለዝና ወይም ድብቅ የሆነ ሌላ የግል ጥቅማቸውን ለማስከበር ለማግኘት እንጅ ለሀገርና ለወገን በማሰብ አንዳች ነገር አድርገው አያውቁም፡፡
እነኝህ ግለሰቦች በሚቃወሙበት ጊዜ ለመቃወማቸው ምክንያት ሲጠየቁ ብዙ ጊዜ ሊያቀርቡት የሚችሉት ምንም ዐይነት ምክንያት የላቸውም፡፡ ካቀረቡም የረባ አይሆንም፡፡ ወይ እራሳቸው አይሠሩትም ወይ ደግሞ ሌላው እንዲሠራው አይፈልጉም አይፈቅዱም፡፡ ሌላው ሠርቶት ሲደነቅ ሲከበር ሲያዩ በሰይጣናዊ የቅናትና የምቀኝነት መንፈስ ቆሽታቸው ይደብናል፡፡ እንኳንና ለልጆቻቸው፣ ለሀገር፣ ለወገን ለራሳቸውም እንኳን ቢሆን ምን ቢሆን እንደሚበጅ በቅጡ የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም፡፡ የሚገርመው ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ ራሳቸውም እንኳን አያውቁትም፡፡ የሚያደርጉት ነገር ከግል ሕይዎታቸው ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ እንደሚጎዳ እንደማይጠቅም እንኳንና እራሳቸው ሊያስቡት ተነግሯቸውም እንኳ አይገባቸውም እንዲገባቸውም አይፈልጉም፡፡ በጣም የሚገርመው እንዲህ ዓይነት ክፉ የቅናትና የምቀኝነት መንፈስ ተማሩ በሚባሉት የሚብስ መሆኑ ነው፡፡ ችግሩ ግን የተማረ ከሚባለው ጀምሮ መሀይም እስከሚባለው ዜጋ ድረስ በየቦታው አለ፡፡ ሥራ እንዳይሠራ ብዙ ያውካሉ፡፡ በተለይ የተማሩ የተባሉቱ ተቃውሟቸውን የትም ሲያቀርቡ ተቃውሟቸው በቂና አሳማኝ ምክንያት ይኖረው ይሆናል በሚል ግምት ብዙ ጊዜ ሕዝብ ይሰናከልና ድጋፍ መስጠት ላለበት አካል ድጋፍ ይነፍጋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ችግር ምክንያት የተቀደሰ ዓላማ ተይዞ ስንት ሊሠሩ የሚሞከሩ በርካታ ሥራዎች ከንቱ ሆነው ይቀራሉ፡፡ የእነዚህን ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ፈተና ተቋቁሞ ሥራ መሥራት የተቀደሰን ዓላማ ከግብ ማድረስ እንደ ዕድል አልፎ አልፎ የሚገኝ እንጅ በብዛት የሚታይ አይደለም፡፡ እናም ከዚህ ችግራቸው የተነሣ ሕዝባዊ ትግሉን የሚቃወሙ ወገኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ የሚያቀርቡት ተቃውሞ ከወያኔነት አንጻር ባይሆንም ቅሉ በሕዝባዊ ትግሉ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከቅጥረኞች የማይተናነስ እንዲያውም የባሰ በመሆኑ እነሱንም እንደ ወያኔ ሁሉ የሀገርና የሕዝብ ጠላት አድርጎ መቁጠርና የሚፈጽሙትንም ጥቃት መከላከል ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
የተያያዝነው ትግል የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡ ጨዋታ አይደለም የተያዘው ሀገርንና ሕዝብን ከጠባብ ጨካኝ ደንቆሮ አንባገነን አገዛዝ መዳፍ ፈልቅቀን ነጻ ለማውጣት ነው እየታገልን ያለነው፡፡ የግድ የሚወሰዱ ቆራጥ አቋሞች ይኖራሉ፡፡ የመረጥነውን የማውረድ መብቱ እያለን የመረጥነውን መንግሥት በኃይል ለማውረድ መሥዋዕትነት የምንከፍልበት ምንም ምክንያት የለንም መርጠን ያስቀመጥነውን መንግሥት ማንም በኃይል እንዲያስወግደው አንፈልግም አንፈቅድምም፡፡ አገዛዙ ያልመረጥነው በመሆኑና በኃይል የተጫነን ይህንን አገዛዝ በምርጫ ልናወርደው ልናስወግደው የሚያስችለን ሥርዓት በፍጹም የሌለ ስለሆነ እንጅ፡፡ ከተረባረብን በእርግጠኝነት ተሳክቶልን በቅርብ ጊዜ ሀገርንና ሕዝብን ነጻ እናወጣለን፡፡ ባለመብሰላችን እየሆነና ሊሆን ያለውን በማስተዋል አቅቶን አርቀንና ግራ ቀኝ መመልከት ተስኖን እያንዳንዳችን መወጣት ያለብንን ግዴታና ኃላፊነት መወጣት ቸግሮን መረባረብ መተባበር ካልቻልን ደግሞ ወያኔ እንደሚለው ለ60 ዓመታት ብቻ አይደለም ለዘለዓለሙ ባልመረጥከውና በኃይል ጫንቃህ ላይ ተጭኖ በነፍስ በሥጋህ እየተጫወተብህ ባለው አገዛዝ በወያኔ የጭቆና ቀንበር ስር ተጠፍንገህ ሰብዓዊ ክብርህን አተህ እየተዋረድክ የባርነት ኑሮህን እየኖርክ ይንንም የውርደት ኑሮ ለልጅህ እያወረስክ ፍዳህን ትቆጥራታለህ! በእርግጠኝነት ይህ እንዲሆን የሚወድና የሚደቅድ ኢትዮጵያዊ አይኖርምና ያለን ብቸኛ አማራጭ መረባረብ ነው እንረባረብ ወገን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው